ውጤቱ የበለጠ ጠንክርን እንድንሰራ ያደርገናል

Published by corporate communication on

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ትራንስሚሽን ሰብስትሽን ኦፕሬሽን የስራ ዘርፍ በሀዋሳ ከተማ   የ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማዊ መካሄዱ ይታወቃል፡፡

በዚህ ግምገማዊ ውይይት  ላይ ከስራ ዘርፉ የላቀ አፈጻጸም  በማስመዝገብ  ለደብብ ምእራብ ሪጂን  እውቅና ተሰጥቷል፡፡

የደብብ ምእራብ ሪጅን ትራንስሚሽን ሰብስትሽን ኦፕሬሽን   ቢሮ ዳይሬክተር  አቶ ጌታሁን  ሲሳይ  ውጤቱን አስመልክቶ  እንደተናገሩት ውጤቱ ስራችን በቀጥይም  በተሸለ ትጋት ጠንክረን  ይበልጥ እንድንሰራ ያደርገናል በለዋል፡፡

ለዚህ ስኬት ካበቁን ስራዎች መካከል የኃይል መቆራጥን ለማስቀረት ችግሩ ምን ላይ ነው የሚል የምርመራ እና የሱፐርቪዥን  ቡድን አቋቁመን ወደ ስራ መግባታችን እና  የምርመራ እና የሱፐርቪዥን ቡድን ስራ የሚያግዝ  አዲስ የሞባይል መተግበሪያ  በራሳችን ባለሞያ  ተሰርቶ ወደ ስራ በመገባቱ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

የሞባይል  መተግበሪያው የሚያጋጥመንን የመስመር እና የማከፋፈያ ችግር ከቦታው ሆኖ ወይም ኔትወርክ  ባለበት አቅራቢያ  ሆነው ስለሚልኩ ችግሩን በአጠረ ግዜ  ለመፍታት እያስቻለ ይገኛል፡፡ ይህም  ውጤት ለማስመዝገብ  እገዛ አድረጎልናል ብለዋል፡፡

የሞባይል መተግበሪያውን የሰራው የደቡብ ምእራብ ሪጅን የማከፋፈያ ጥገና ባለሞያ  አቶ ማእሩፍ ሚፍታህ  እንደተናገሩት  የምርመራ (inspection ) ስራው በወረቀት ላይ የተመሰረተ እና  ሪፖርት ለማቅረብ ረጅም ጌዜ የሚወስድ እና የዳታ ጥራት ችግር እንደ አለበት በመረዳት መተግበሪያውን መስራቱን ተናግሯል፡፡

ሰብስቴሽን  ኢንሰቴክሽን እና ትራንስሚሽን ኢንስፔክሽን  የሚባሉ ሁለት መተግበሪያዎችን መስራቱን የገለጸው  አቶ ሚፍታህ እነዚህን ለመስራት አራት ወራት ወስዶብኛል ብሏል፡፡

ወደ ተቋሙ ከተቀጠረ አንድ አመት እየሞላው የሚገኘው  አቶ ሚፍታህ መተግበሪያውን በቀሩት ሪጅኖችም እንዲተገበር ስልጠና መስጠቱን ጨምሮ አስረድቷል፡፡  

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

16 − two =