ዋና ስራ አስፈፃሚው ግልገል ጊቤ 2 የውሃ ኃይል ማመንጫን ጎበኙ

Published by corporate communication Editor on

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፋፃሚ ዶ/ር አብርሃም በላይ ግልገል ጊቤ 2 የውሃ ኃይል ማመንጫን ጎበኙ።

ዋና ስራ አስፈፃሚው በጉብኝታቸው ከማመንጫው ሰራተኞች ጋር ተወያይተዋል።

የዋና ስራ አስፈፃሚው ጉብኝት የኃይል ማመንጨት የኦፕሬሽን ስራዎች በውጤታማነትና በቅልጥፍና እንዲከናወኑና ሰራተኞችም የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማድረግ ዓላማ አለው።

የኦፕሬሽን ስራዎች በአስቸጋሪና አደገኛ የስራ ሁኔታ ውስጥ የሚከናወኑ በመሆናቸው የተቋሙ ሰራተኞች ላሳዩት ጽናትና ለከፈሉት መስዋዕትነት ያላቸውን አድናቆት ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል።

የጣቢያው ሰራተኞች የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተው ምላሽ ተሰጥቷቸዋል።

03/08/2011 ዓ/ም

Categories: ዜና

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

nineteen − 5 =

Facebook