ዋና ሥራ አስፈፃሚው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት በመጠናቀቁ ለመላው የድርጅቱ ሠራተኞችና አመራሮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው በመልዕክታቸው የግድቡን ቀሪ ስራ ለማጠናቀቅ በቀጣይ ፈታኝ ሥራዎች የሚጠበቁ በመሆኑ ሥራው በታላቅ ቁርጠኝነት እና ትጋት እንዲቀጥል አሳስበዋል።
የፕሮጀክቱን ማኔጅመንት፣ ተቋራጮችና አማካሪዎች እንዲሁም ከሁሉም በላይ ሳምንቱን ሙሉ ቀንና ለሊት 24 ሰዓት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እየሰሩ ፕሮጀክቱን ለዚህ ስኬት ያበቁ ሰራተኞችን አመስግነዋል።
ለፕሮጀክቱ እውን መሆን ህይወታቸውን መስዋዕት ያደረጉ ሰራተኞችንም ተቋሙና ህዝብ ፕሮጀክቱ ጋር ሲያስታውሳቸው እንደሚኖር ጠቅሰዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለፕሮጀክቱ ስኬት ለሰጡት አመራር፣ ክትትልና ድጋፍ ምስጋና ይገባቸዋል ያሉት ሥራ አስፈፃሚው ለውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ስለሺ በቀለ፣ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ እና ለመከላከያ ሠራዊትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
0 Comments