ዋና ሥራ አስፈፃሚው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራዎችን ጎበኙ

Published by corporate communication Editor on

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢንጂነር አብርሃም በላይ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን ጎበኙ፡፡

የዋና ስራ አስፈፃሚው ጉብኝት ዓላማ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ውስጥ በመሳተፍ ላይ ያሉ ተቋራጮች የያዙትን ስራ ለመከታተልና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ነው፡፡

ከግድቡ መጠናቀቅ አስቀድሞ ኃይል የሚያመነጩትን ዩኒቶች ወደስራ ለማስገባት ተቋራጮቹን በየጊዜው በስራ ላይ መከታተል፣ እንዲሁም ወቅታዊ ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባ በመንግስት አቅጣጫ መቀመጡን ዶ/ር አብርሃም አስታውሰዋል፡፡

ተቋራጮቹን በቅርበት መከታተል ያስፈለገውም ፕሮጀክቱ በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንዲከናወን ለማድረግና ለሚፈጠሩ ክፍተቶች አፋጠኝ መፍትሔ ለመስጠት እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡

አሁን እየተሰሩ ያሉት ስራዎች በታህሳስ 2013 ዓ.ም. የቅድመ ማመንጨት ስራዎችን ለማጠናቀቅና በ2015 ዓ.ም. ደግሞ ግንባታውን ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ እንደሆነ መመልከታቸውን ዋና ሥራ አስፈፃሚው ዶ/ር አብርሃም ገልፀዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚው የፕሮጀክቱን ስራ በቅርበት ሲጎበኙ በአንድ ወር ውስጥ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡

Categories: ዜና

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

10 + seven =

Facebook