ዋና ሥራ አስፈፃሚውና አምባሳደሩ የመልካ ዋከና የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያን ጎበኙ

Published by corporate communication on

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር የመልካ ዋከና የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያን ጎበኙ፡፡

ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ አሸብር ባልቻ ጣቢያው ከ30 ዓመት በላይ ያገለገለ በመሆኑ የማሻሻያ ሥራዎች እንደሚፈልግ ለአምባሳደሩ ገልፀውላቸዋል፡፡

የጣቢያውን አቅም ለማሳደግ ቀደም ሲል የመግባቢያ ሥምምነት መፈረሙን በማስታወስ የተጀመሩት ቴክኒካል ጥናቶች ሂደቶች እንዲፋጠኑና ለማሻሻያ ስራው ሩሲያ አስፈላጊውን ድጋፍ እንድታደርግ ጠይቀዋል፡፡

አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪን በበኩላቸው በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ካምፓኒ ለተገነባው የኃይል ማመንጫ ጣቢያ የማሻሻያ ሥራ ሩሲያ አስፈላጊውን እንደምታደርግ አረጋግጠዋል፡፡

በጉብኝቱ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አምባሳደር ሌንጮ ባቲና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

የመልካ ዋከና የኃይል ማመንጫ ጣቢያ 153 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው በ1980 ዓ.ም  ነበር፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

six + nine =