ከደብረታቦር እስከ ነፋስ መውጫ የሚገኘው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

Published by corporate communication on

በአሸባሪው የህወኃት ቡድን ጥቃት የደረሰበት ከደብረታቦር እስከ ነፋስ መውጫ የሚገኘው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተጠግኖ ከትናንት ምሽት ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

ከደብረታቦር ነፋስ መወወጫ ድረስ ባለው መስመር ላይ በተፈፀመ ጥቃት የኃይል ማስተላለፊያ ሽቦ(ኮንዳክተር) በተለያዩ 13  አካባቢዎች ላይ በመበጣጠሱ ኃይል ተቋርጦ ቆይቷል።

መስመሩን እንደአዲስ በመቀየርና እና መገናኘት የሚችሉትን የተለያዩ መገናኛዎችን በመጠቀም ለመጠገን ከፍተኛ ርብርብ ተደርጓል።

 የደረሱትን ጉዳቶች በመጠገን በትናንትናው ዕለት ነሐሴ 28 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽት 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ንፋስ መውጫና ደብረታቦር ከተሞችና አካባቢያቸው ኃይል እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል፡፡

የንፋስ መውጫ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በሽብርተኛው ቡድን ዘረፋና የንብረት ማውደም ቢፈፀምበትም ዳግም በማደስ ለአገልግሎት ማብቃት ተችሏል።

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

19 + 19 =