ከወላይታ ሶዶ-አዲስ አበባ የተዘረጋው ሁለተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር አገልግሎት መስጠት ጀመረ

Published by corporate communication on

ከወላይታ ሶዶ-አዲስ አበባ የተዘረጋው ሁለተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር በነባሩ የጊቤ III- ወላይታ ሶዶ- አዲስ አበባ ታወር ወይም ማማ ላይ በተጨማሪ የተዘረጋ መሆኑን የ400 ኪ.ቮ ፕሮጀክት ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ መሐመድ ሽኩር ተናግረዋል፡፡

በፕሮጀክቱ በዋናነት የኤሌክትሪክ ኮንዳክተር እና ኢንሱሌተር ዝርጋታ እንዲሁም የተለያዩ መሳሪያዎች ገጠማ መከናወኑን ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡

እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለፃ የተዘረጋው ሁለተኛ መስመር በነባሩ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ይስተዋል የነበረውን የኃይል መጨናነቅ በማስቀረት አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ ያግዛል፡፡

የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ 400 ኪ.ቮ የኤሌክትሪክ ኃይል የመሸከም አቅም ያለው እና 260 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ሲሆን ግንባታውን ለማከናወን 7 ነጥብ 8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እና 43 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል፡፡

የፕሮጀክቱን ግንባታ የቻይናው ሻንጋይ ኤሌክትሪክ ኩባንያ ያከናወነው ሲሆን የዚህ ፕሮጀክት አካል የሆነው የጊቤ III- ወላይታ ሶዶ ሁለተኛ መስመር ዝርጋታ ለማከናወን በሂደት ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

15 + sixteen =