ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ችግኝ እንዲያፈሉ ይደረጋል- በተቋሙ የጄኔሬሽን ኦፕሬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ አንዳርጌ እሸቴ

Published by corporate communication on

በጊቤ 3 የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የሠራተኞች መኖሪያ ካምፕ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተከናውኗል፡፡

በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉት የኃይል ማመንጫዎች ኦፕሬሽን ሥራ አስፈፃሚ አቶ አንዳር እሸቴ እንደተናገሩት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ስራ የሀገሪቱን የውሃ ሀብት በማሻሻል ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡

የአርንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ በአፈር መሸርሸር ምክንያት ደለል ወደ ውሃ ኃይል ማመንጫ ግድቦች እንዳይገባ በማድረግ ጣቢያዎቹ ለበርካታ ዓመታት እንዲቆዩ ያግዛል ብለዋል፡፡

እንደ አቶ አንዳርጌ ገለፃ በእያንዳንዱ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ከ1000 በላይ ችግኞች ለመትከል እቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው፡፡

በቀጣይ ዓመትም በሁሉም ማመንጫ ጣቢያዎች ኃይል ሀገር በቀል ችግኞችን ለማፍላት እቅድ መያዙን አቶ አንዳርጌ ገልፀዋል፡፡

ይህም ለአካባቢው ስነ- ምህዳር ተስማሚ የሆነ ችግኝ ለመትከል ያግዛል ነው ያሉት፡፡

በኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ላይ ከዚህ በፊት ችግኝ የመትከል ስራ ሲከናወን የነበረ ቢሆንም በመንከባከብ ስራው ላይ ግን ክፍተት በመኖሩ የተተከሉ ችግኞች እንዲጸድቁ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ነው የተናገሩት፡፡

በማመንጫ ጣቢያ ሠራተኞች ከሚከናወን የችግኝ ተከላ ስራ በተጨማሪ በአንዳንድ ጣቢያዎች አካባቢ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ የአረንጓዴ አሻራ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝም አስታውቀዋል፡፡

“ዛፍ የህይወት መሰረት ነው” ያሉት አቶ አንዳርጌ ሁሉም ስነ -ምህዳርን መንከባከብ አስፈላጊ መሆኑን ተገንዝቦ ራሱንና ቤተሰቡነ ከኮሮና ቫይረስ በመከላለክ የአረንጓዴ አሻራ ስራን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

የጊቤ 3 የውሃ ኃይል ማንጫ ጣቢያ ስራ አስኪያጅ አቶ ሃብታሙ ሰሙ በበኩላቸው ጣቢያው የሚገኝበት አካባቢ በደን የተሸፈነ በመሆኑ ከዚህ በፊት የተተከሉትንም በመንከባከብ ስራ ላይ ትኩረት ይደረጋል ብለዋል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

3 × two =