ኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒግ (ኢ.አር.ፒ) የአሰራር ሥርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ያስፈልጋል ተባለ

Published by corporate communication on

ኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒግ (ኢ.አር.ፒ)  የአሰራር ሥርዓትን በተቋሙ ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉም የሥራ ክፍሎች የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሞደርናይዜሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ኃላፊ አቶ ገነቱ ደሳለኝ እንደገለፁት ተቋሙ ያሉትን ሀብቶች በአንድ የመረጃ ቋት ውስጥ መዝግቦ ለማስተዳደር የኢ.አር.ፒ ሚና ከፍተኛ ነው፡፡

በአሁኑ ሰዓት በተቋሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የአሰራር ሥርዓት ለመዘርጋት ዝግጅት እየተደረገ በመሆኑ የደረጃው ያሉ የሥራ ክፍሎች በባለቤትነት ስሜት በትብብር ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

የአሰራር ሥርዓቱን ለመተግበር ከሀብት ምዝገባ ጋር የተያያዙ የመረጃ ክፍተቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ የጠቆሙት ኃላፊው ችግሩን ለመቅረፍም ሁሉም የሥራ ክፍሎች በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

እንደ አቶ ገነቱ ገለፃ ኢ.አር.ፒ የአሰራር ሥርዓት ሁለንተናዊ የሆነ ተቋማዊ ለውጥ ከማምጣት ባሻገር መረጃዎችን በአግባቡ በመመዝገብ የሀብት ብክነትን ያስቀራልም፡፡

ኢ.አር.ፒ የአሰራር ሥርዓት የፋይናንስና ቁጥጥር፣ የሰው ሀብትና ፔሮል፣ የመረጃ ማዕከል፣ የንብረት አስተዳደርና የዕቃ ግምጃ ቤት እንዲሁም መሰል አስተዳደራዊ ሞጁሎች ያሉት ዘመናዊ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሳፕ ከተባለው የጀርመን ሶፍትዌር አምራች ኩባንያ  የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒግ (ኢ.አር.ፒ) የአሰራር ሥርዓት ሶፍትዌር ፈቃድ ለመግዛት በሂደት ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጋር የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒግ (ኢ.አር.ፒ) የአሰራር ሥርዓት መሰረተ ልማት ዝርጋታና አቅም ግንባታ ሥምምነት በትናንትናው ዕለት መፈራረሙን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

five + 1 =