ኢትዮ – ኤሌክትሪክ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማደጉን አረጋገጠ
ኢትዮ – ኤሌክትሪክ ጌዲዮ ዲላን በመርታታት ወደ ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መመለሱን አረጋገጠ።
ወደ ፕሪሚየር ሊግ ለመግባት በሶስት ምድብ ተከፍሎ በከፍተኛ ሊግ ውድድር ሲካሄድ ነበር፡፡
ዛሬ ረፋድ ላይ ባህር ዳር ላይ በተደረገ የ17ኛ ሳምንት ጨዋታ ኢትዮ – ኤሌክትሪክ ጌዲዮ ዲላን 2-0 መርታቱን ተከትሎ አንድ ጨዋታ እየቀረው ወደ ፕሪምየር ሊጉ መመለሱን አረጋግጧል።
ኢትዮ – ኤሌክትሪክ ወደ ፕሪሚየር ሊግ የሚያድግ ከሆነ ለበቡድኑ 10 ሚሊየን ብር ለመሸለም ቃል መግባቱን መዘገባችን ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ የአመራር ቡድን በተገኘው ድል የተሰማውን ደስታ እየገለፀ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
0 Comments