ኢትዮ ቴሌኮም በ8100 የሰበሰበውን ገንዘብ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዛሬ ያስረክባል

Published by corporate communication on

ኢትዮ ቴሌኮም በ8100 አጭር ቁጥር ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሰበሰበውን ገንዘብ ዛሬ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሊያስረክብ ነው።

ኢትዮ ቴሌኮም ከታላቁ የኦትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በ8100 አማካይነት ለግድቡ ግንባታ የሚውል ገንዘብ ከደንበኞ ቹ ሲያሰባስብ መቆየቱ ይታወሳል።

በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የመገናኛ ብዙሃን በተገኙበት የርክክብ ስነስርዓቱ የሚከናወን ይሆናል።

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

twelve − 7 =