ኢትዮጵያ በቀጣዩ ክረምት ህጋዊና ቴክኒካዊ አካሄዶችን ተከትላ ውሃ ትይዛለች

ኢትዮጵያ በቀጣዩ ክረምት ህጋዊና ቴክኒካዊ አካሄዶችን ተከትላ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ እንደምትይዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አረጋገጡ፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ዓባይን አልገደበም፤ ወደፊትም አይገድብም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ የወንዙ ተፈጥሮኣዊ ፍሰት ሳይቋረጥ በክረምት ወራት ከፍተኛ ዝናብ ስለሚዘንብ ዘንድሮም ውሃውን እንይዛለን ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በሰጡት ማብራሪያ እንደገለፁት በክረምት ወራት ውሃውን ሳይሞሉ ማለፍ ሀገሪቱን አንድ ቢሊዮን ዶላር ሀገሪቱን ያሳጣታል፡፡
የኢትዮጵያ ፍላጎት ግብፅና ሱዳንን መጉዳት ሳይሆን በወንዙ በመጠቀም ከጭለማ መውጣት ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
የውሃ አሞላሉን በተመለከተም ኢትዮጵያ ዛሬም ቢሆን ድርድሩን ለመፈረም ዝግጁ መሆኗን አስታውቀዋል፡፡
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ለኢትዮጵያ ህዝብ በገባነው ቃል መሰረት እናሳካዋለን ሲሉ ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡
0 Comments