ኢትዮጵያን እናልብስ መርሃ ግብር በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ተጠሪ ተቋማቱ ሠራተኞች በይፋ ተጀምሯል

Published by corporate communication on

የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴርና የአስሩ ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች በኢትዮጵያን እናልብስ መርሃ ግብር 10 ሺህ ችግኞችን ተክለዋል።

የችግኝ ተከላ መርሃግብሩ  ዛሬ ማለዳ በፊንፊኔ ልዩ ዞን በረህ ወረዳ ሲሬ ጉዮ ቀበሌ ገበሬ ማህበር በለገዳዲ የውሃ ማጣሪያ ግድብ አካባቢ ተካሂዷል፡፡

 “ኢትዮጵያን እናልብስ” በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው 3ኛው ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ላይ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለን ጨምሮ  የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የተጠሪ ተቋማቱ የስራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች  ተሳትፈዋል።

ችግኙ የተተከለበት አካባቢ ለአዲስ አበባ የውሃ አቅርቦት ከሚሰጡ የውሃ መገኛዎች መካከል አንዱ ነው፡፡

መርሃግብሩን ያስተባበሩት የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድርና የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በጋራ በመሆን ነው፡፡

በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በአራት ዓመት 20 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ግብ ተቀምጦ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የራሱን አሻራ እያሳረፈ ይገኛል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

two × 1 =