ኢትዮጵያና ጅቡቲ የነበራቸውን የኃይል ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ

Published by corporate communication on

ኢትዮጵያና ጅቡቲ በመካከላቸው ያለውን የኃይል አቅርቦት ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ፡፡

በኢፌዲሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ የተመራና የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተ ልዑካን ቡድን ከጅቡቲ አቻው ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

በውይይቱም ግንባታው እየተገባደደ ካለው የአይሻ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የሚመነጨውን የኤሌክትሪክ ሀይል ከኢትዮጵያ ወደ ጂቡቲ ከተዘረጋው የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ጋር ለማገናኘት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

የሚሰራውን ሥራ በተመለከተም አንድ የውጭ ድርጅት በጋራ በመምረጥ ለማስጠናት ከመግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡

በሀገራቱ መካከል ያለውን የኃይል ትስስር የበለጠ ለማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በትብብር ለመስራት ያላቸውን ጽኑ አቋም በመግለፅ በዘርፉ የሚደረገውን ቀጣይ ውይይት በአዲስ አበባ ለማድረግ  ተስማምተዋል፡፡

በሶማሌ ክልል ሺኒሌ ዞን አይሻ ወረዳ እየተገነባ ያለው የአይሻ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት እያንዳንዳቸው 2 ነጥብ 5 ሜጋ ዋት የሚያመነጩ 48 ተርባይኖች ያሉት ሲሆን እስከ 120 ሜጋ ዋት ሀይል የማመንጨት አቅም ያለው ነው።

ፕሮጀክቱ በ257 ነጥብ 2 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡

ምንጭ – በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የማህበራዊ ትስስር ገፅ

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

five × three =