አስተማማኝ ተጨማሪ ኃይል ለማቅረብ የሚያስችል አቅም ተፈጥሯል

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የደቡብ ሪጅን ትራንስሚሽን ሰብስቴሽን ኦፕሬሽን ቢሮ በማኝናውም መልኩ ለሚመጣ የተጨማሪ የኃይል አቅርቦት ጥያቄን ለመመለስ የሚያስችል አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት አቅም እንዳለው ገለጸ፡፡
የቢሮው ዳይሬክተር አቶ አለማየው አበጋዝ እንደተናገሩት ሪጅኑ ሁለት ባለ 400 ኪ.ቮ፣4 ባለ 230 ኪ.ቮ እና 13 ባለ 132 ኪ.ቮ የሆኑ 19 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ያስተዳድራል፡፡
በእነዚሁ ማከፋፋያ ጠቢያዎች በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉት የማሻሻያ እና የማስፋፈያ ሥራዎች የኃይል አቅርቦት አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ ማሣደጉን ተናግረዋል፡፡
ሪጅኑ ከግቤ 3 እና ከገናሌ ዳዋ 3 ኃይል ማንመጫ ጣቢያዎች ኃይል በቀጥታ ይቀበላል፡፡በመሆኑም ሪጅኑ ከሚደርስባቸው የህብረተሰብ ክፍሎችና ከግል ባለ ሀብቶች የሚመጣን የተጨማሪ የኃይል አቅርቦት ጥያቄ በበቂ ሁኔታ ለማስተናገድ የሚያስችል አቅም እንዲኖረው ማስቻሉን አቶ አለማየው ተናግረዋል፡፡
ሪጅኑ ከኦሮሚያ ክልል ምእራብ አርሲን ፣ ሻኪሶን፣ ቦረና ዞኖች እና ከደቡብ ክልል ጌዶን፣ ወላይታን በሀላባን ዞኖች እና የሲዳማ ክልልን ሙሉ ለሙሉ እንዲሁም ሀዲያ- ሆሳእና ዞንን በከፊል በማድረስ በአሁን ወቅት 60 ሜጋ ዋት ኃይል ያቀርባል ፡፡
እነዚህን በተለያዩ አቅጣጫ የሚገኙትን አካባቢዎች በማስተሳሰር ኃይል ለመስጠት 3,200 ኪ.ሜትር ርዝመት ያለው የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች በተለያየ የቮልቴጅ መጠን ተዘርግተው አግልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ዳሬክተሩ ጠቁሟል፡፡
0 Comments