ኃይል የማመንጨት ሥራውን ለማዘመን እየተሰራ ነው

Published by corporate communication on

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ላይ የተለያዩ የማዘመን ሥራዎችን እየተከናወኑ መሆኑን በተቋሙ የኃይል ማመንጫዎች ኦፕሬሽን ሥራ አስፈጻሚ አስታወቁ፡፡

ሥራ አስፈፃሚው አቶ እያየሁ ሁንዴሳ እንደተናገሩት ኃይል የማመንጨት ሥራዉን በዘመናዊ መንገድ ለማከናወን በማመንጫ ጣቢያዎች ላይ የተለያዩ የማዘመን ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

በአሁኑ ሰዓትም በግልገል ጊቤ 2 የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የዕለት ተዕለት ስራዎችን፣ የቁጥጥር ሥርዓቱን እና ቴክኒካል የሆኑ የድጋፍ ስራዎችን ዘመናዊ በሆን መልኩ እንዲከናወኑ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸው ብለዋል፡፡

እንደ ሀገር የኤሌክትሪክ ኃይል በሚቋረጥበት ጊዜ ከጊቤ 3 እስከ ገላን ድረስ የተዘረጉትን መስመሮች እና የጣቢያው ዩኒቶች በማኑዋል ሲፈተሹ እንደነበር ያነሱት ሥራ አስፈፃሚው በአሁኑ ሰዓት ስራውን አውቶማቲክ በሆነ መልኩ ለማከናወን የማዘመን ስራ ለማከናወን እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ይህንንም ሥራ ለማከናወን 420 ሺህ ዶላር በጀት ተይዞ ዶንግ ፋንግ ከተሰኘ የቻይና ኩባንያ ጋር የውል ስምምነት መፈረሙንም ሥራ አስፈፃሚው ገልጸዋል፡፡

አቶ እያየሁ አክለውም በጊቤ 1 እና በበለስ የውኃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ላይ የስካዳ ማሻሻያ ስራዎችን ለማከናወን የስምምነት ድርድር በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የተለያዩ የማዘመን ስራዎች እየተከናወነላቸው ከሚገኙ ማመንጫ ጣቢያዎች በተጨማሪ በቀጣይ በሌሎች ጣቢያዎች ላይ የማመንጨት ሥራውን ሊያዘምኑ የሚችሉ የተለያዩ ሥራዎችን ለማከናወን እየተሰራ እንደሚገኝ ሥራ አስፈጻሚው አስታውቀዋል፡፡

የኃይል ማመንጫዎች ኦፕሬሽን የቴክኒክ ድጋፍ ሥራ አስኪያጁ አቶ አብዱ ይማም በበኩላቸው እንደገለፁት በጣቢያው ላይ ከዕቅድ ጀምሮ የመለዋወጫ እቃ አቅርቦቱን፣ የዕቃ ግምጃ ቤት አስተዳደርን፣ የመረጃ አያያዝ እና ሪፖርት የማድረግ ስራዎችን (on care asset management system) በዘመናዊ መልኩ እንዲከናወን ለማድረግ የሚያግዙ የተለያዩ ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸው፡፡

እንደ አቶ አብዱ ገለጻ በጣቢያው ላይ ትክክለኛ ያልሆነ ድምጽ ሲሰማ ያለውን ችግር በቀላሉ መለየት እንዲቻልና የጣቢያውን የቁጥጥር ስርዓት ማዘምን የሚያስችል “On care acoustics” ስራ እየተከናወነ ይከኛል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ቴክኒካል የሆኑ የድጋፍ ስራዎችን በምስል በተደገፈ መልኩ (On call video) ከሌላ አካባቢ ከርቀት ሆኖ እንዲከናወኑ ለማድረግ የሚያግዝ የማዘመን ስራ እየተከናወነ መሆኑን ሥራ አስኪያጁ ጠቁመዋል፡፡

በጊቤ 2 ማመንጫ ጣቢያ ላይ እየተከናወነ ያለው የማዘመን ሥራ ከጀርመን መንግስት በድጋፍ የተገኘ ከ677 ሺህ ዩሮ በላይ በጀት ቮይት (Voith) በተባለ የጀርመን ኩባንያ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

መጋቢት 2013 ዓ.ም አካባቢ የተጀመረው ይህ ፕሮጀክቱ በአሁኑ ወቅት በመጠናቀ ላይ ሲሆን የኮሚሽኒንግ ስራውን በቅርቡ ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

15 − 4 =