ኃይል ማስተላለፍ
ኃይል ከማመንጨት ባሻገር የመነጨውን የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ብሔራዊ የኃይል ቋት ለማስተላለፍ የሚረዱ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያና ማከፋፈያ ጣቢዎች በመላ ሀገሪቱ ተገንብተዋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ ከ132 እስከ 500 ኪሎ ቮልት አቅም ያላቸው ከ20‚000 ኪ.ሜ በላይ ሰርኪዩት ርዝመት ያላቸው የከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ተገንብተዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል ባለ 500 ኪሎ ቮልት የህዳሴ – ዴዴሳ – ሆለታ፤ ባለ 500 ኪሎ ቮልት የኢትዮ – ኬንያ፣ ባለ 400 ኪሎ ቮልት የወላይታ ሶዶ II-አዲስ አበባ፤ባለ 230 ኪ.ቮ የቆቃ – ሁርሶ – ድሬዳዋ፤ ባለ 230 ኪ.ቮ ሀላባ – ሆሳዕና – ግልገል ጊቤ 2 – ጅማ – አጋሮ – በደሌ እና ባለ 230 ኪሎ ቮልት መቱ – ጋምቤላ ይጠቀሳሉ፡፡
በተጨማሪም 186 የተለያዩ የቮልቴጅ መጠን ያላቸው የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ግንባታ ሥራዎች ተጠናቀው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡
Number of substations by voltage level (kV) | |||||
---|---|---|---|---|---|
Year (G.C) | 400 | 230 | 132 | Total | |
500 | |||||
2017/18 | 2 | 11 | 51 | 91 | 155 |
2018/19 | 2 | 12 | 54 | 95 | 163 |
2019/20 | 2 | 14 | 59 | 100 | 175 |
2020/21 | 2 | 16 | 63 | 101 | 181 |
2021/22 | 3 | 16 | 64 | 103 | 186 |