ኃይል ማመንጨት

ኃይል ማመንጨት

ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ፈጣንና ተከታታይ ዕድገት ማስመዝገብ ችላለች፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል ልማት ደግሞ ለዚህ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዕድገት ጉልህ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን ለማቋቋም በወጣውና በተሻሻለው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 381/2008 መሠረት ተቋሙ የኃይል ማመንጫዎችን፣ የኃይል ማስተላለፊያዎችንና የኃይል ማከፋፈያዎችን የመገንባት፣ የጅምላ ሽያጭ፣ የተስማሚነት ጥናት፣ የዲዛይንና የቅየሳ ሥራ የማከናወን ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ተቋሙ 22 የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን በማስተዳደር ላይ ይገኛል፡፡ ከእነዚህም መካከል 16 ያህሉ ከውሃ ሲሆኑ እነሱም ጊቤ 3 (1870 ሜ.ዋ)፤በለስ (460 ሜ.ዋ)፤ ግልገል ጊቤ 2 (420 ሜ.ዋ)፣ ተከዜ (300 ሜ.ዋ)፣ ግልገል ጊቤ 1 (184 ሜ.ዋ)፣ መልካ ዋከና (153 ሜ.ዋ)፣ ፊንጫ (134 ሜ.ዋ)፣ አመርቲ ነሼ (95 ሜ.ዋ)፣ ጢስ ዓባይ 2 (73 ሜ.ዋ)፣ ቆቃ (43.2 ሜ.ዋ)፣ አዋሽ 2 (32 ሜ.ዋ)፣ አዋሽ 3 (32 ሜ.ዋ)፣ ጢስ ዓባይ 1 (11.4 ሜ.ዋ) አባ ሳሙኤል (6.6 ሜ.ዋ)፤ ገናሌ ዳዋ 3 (254 ሜ.ዋ.) እና ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ( ሥራ የጀመሩት ሁለት ዪኒቶች 750 ሜ.ዋ.) በድምሩ ከውሃ 4818.2 ሜጋ ዋት ያመነጫሉ፡፡

ከንፋስ ደግሞ አዳማ 2 (153 ሜ.ዋ)፣ አሸጎዳ (120 ሜ.ዋ) እና አዳማ 1 (51 ሜ.ዋ) እንዲሁም በከፊል ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የአይሻ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ (80 ሜ.ዋ) በድምሩ 404 ሜጋ ዋት በማመንጨት ላይ ሲሆን ቀሪው ከእንፋሎትና ከዲዝል መጠባበቂያ ይገኛል ተብሎ የሚጠበቀው ነው፡፡

የማመንጨት አቅም በሜጋ ዋት (በ2014 ዓ.ም)