ኃይል መሸጥ

ኃይል መሸጥ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከተሠማራባቸው ተልዕኮዎች ውስጥ አንዱ የኤሌክትሪክ ኃይልን በማምረት ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣132 ኪ.ቮ እና ከዚያ በላይ ኃይል ለሚጠቀሙ ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች እና ለጎረቤት ሃገራት በጅምላ የኤሌክትሪክ ኃይል ማቅረብ ነው፡፡

በዚህም ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትም ሆነ ለኢንዱስትሪዎች ኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከጎረቤት ሃገራት መካከልም ከሱዳንና ጂቡቲ ጋር የኃይል ትስስር በመፍጠር እና በአማካኝ ከ100 ሜጋ ዋት ያላነሰ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ በአማካኝ በየአመቱ 70 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በማስገኘት ላይ ነው፡፡

በተጨማሪም ሃገራችንን ከምስራቅ አፍሪካ ባሻገር የአፍሪካ የኃይል ምንጭ ማዕከል በማድረግ የክፍለ አህጉሩን የኢኮኖሚና ማህበራዊ ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ከሌሎች ጎረቤት ሃገራት ጋር የኃይል ትስስር በመፍጠርና በማጠናከር ወደ ክፍለ አህጉራዊ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ሲሆን ለአብነትም የኢትዮ-ኬንያ ባለ 500 ኪ.ቮ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ አንዱ ማሳያ ነው፡፡

በረጅም ጊዜ ዕቅድም ኢትዮጵያ ከሶማሌ ላንድ፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ እና ደቡብ ሱዳን ጋር የኤሌክትሪክ ኃይል ትስስር ለመፍጠር የሁለትዮሽ ግንኙነት በማድረግ ላይ ትገኛለች። በዚህም በቀጣይ ለእነዚህና ለሌሎች ሃገራት በቂ ኤሌክትሪክ ኃይል ኤክስፖርት በማድረግ ለሃገሪቱ የውጪ ምንዛሬ ከሚያስገኙ ተቋማት መካከል አንዱ ዘርፍ ለማድረግ ሰፊ ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸው፡፡