ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም 78 ነጥብ 3 በመቶ ደረሰ

Published by corporate communication on

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም 78 ነጥብ 3 መድረሱን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ገለፁ።

ሚኒስትሩ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑትን ተግባራትና የህዳሴ ግድብን የግንባታ ሂደት በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ዶክተር ስለሺ በመግለጫቸው እንዳመለከቱት የግድቡ ግንባታ የሲቪል ስራዎች አፈጻጸም 91 በመቶ ደርሷል።

አጠቃላይ የግድቡ ግንባታ አፈጻጸም ደግሞ 78 ነጥብ 3 በመቶ መድረሱን አመልክተዋል።

በቀጣይ ወራት የግድቡን ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ለማሳካት እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

ግድቡ ለተፋሰሱ አገሮች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው የተናገሩት ኢንጂነር ስለሺ፤ “የግድቡ ግንባታ ሰኔ ወር ላይ ከነበረበት አፈጻጸም የ4 ነጥብ 05 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

two + seven =