ተጨማሪ ኃይል ለማቅረብ ዝግጁ ሆነን እየጠበቅን ነው

ከአዲስ አበባ በ275 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ የሚገኘው የሀዋሳ 2 ባለ 230/132/33/15 ኪ.ቮ. ከፍተኛ ማከፋፈያ ጣቢያ አገልግሎቱን ሳያቋርጥ እየሰጠ ይገኛል፡፡
በ2011 ዓ.ም አገልልግሎት መስጠት የጀመረው ማከፋፈያ ጣቢያው 20 ባለ 33 ኪ.ቮ. እና 8 ባለ 15 ኪቮ ወጪ መስመሮች እንዳሉት የጣቢያው ተወካይ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ይልማ ተናግረዋል፡፡
እንደ ተወካዩ ገለጻ ከአዋሳ1 ማከፋፈያ ጣቢያ በ132 ኪ.ቮ. ኃይል በመቀበል በሁለት በባለ 15 ከ.ቮ. ወጪ ለአዋሳ ከተማ እና በሁለት በባለ 33 ኪ.ቮ ወጪ ለሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በተገቢው ሁኔታ አየሰጠ ይገኛል ብለዋል፡፡
ማከፋፈያ ጣቢያው በ6 ባለ 15 ኪ.ቮ. እና በ18 ባለ 33 ኪ.ቮ ወጪ መስመሮች ተጨማሪ ከፍተኛ ኃይል ለማቅረብ ዝግጁ ሆኖ ደንበኞችን እየተጠባበቀ እንደሚገኝ አቶ አሸናፊ ጠቁመዋል፡፡
ማከፋፈያ ጣቢያው ባሉት ትራንስፎርመሮች ከአዋሳ1 የሚቀበለውን 132 ኪ.ቮ. ኃይል ወደ 230 ኪ.ቮ. በማሳደግ እየተጠቀመ እንደሚገኝ የገለጹት ተወካዩ እየተገነባ የሚገኘው የይርጋለም2 -ሀዋሳ2 ባለ 230 ኪ.ቮ. ኃይል ማስተላፊያ መስመር ዝርጋታ በቅርቡ ሲያልቅ በቀጥታ ባለ 230 ኪ.ቮ. ኃይል ለመቀበል ያስችለዋል ብለዋል፡፡
በቀጣይም ማከፋፈያ ጣቢያው ለሻሸመኔ እና ለሀላባ ማከፋፈያ ጣቢያዎች በ132 ኪ.ቮ ኃይል ለመስጠት የተለያዩ የዲዛይን ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
0 Comments