ተቋሙ የ2014 አንደኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ገመገመ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ ሥራ አመራር የተቋሙን የአንደኛ ሩብ ዓመት የሥራ እንቅስቃሴ ገምግሟል፡፡
ከጥቅምት 9 ጀምሮ ለሶስት ቀናት በተደተገው ግምገማ የስራ ክፍሎች በሩብ ዓመቱ ያከናወኗቸውን ተግባራት፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎችን በዝርዝር ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
ከኦፕሬሽን ስራዎች አኳያ በኃይል ማመንጫዎች፣ ማስተላለፊያና ማከፋፈያ ጣቢያዎች በኩል የኦፕሬሽን፣ ኢንስፔክሽንና ጥገና ሥራዎች በሩብ ዓመቱ የተሻለ አፈፃፀም እንደነበራቸው በግምገማው ላይ ተጠቅሷል፡፡
በግንባታ ላይ የሚገኙት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ፣ የኮይሻ፣ የአሉቶ የእንፋሎት ኃይል ማመንጫ፣ የአይሻ የንፋሽ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ዕቅድ መሰረት ግንባታቸው በመከናወን ላይ ነው፡፡ ቀሪ ሥራዎችን ከተቀመጠላቸው ጊዜ አንፃር ተጣጥመው እንዲሰሩ አቅጣጫ የተሰጠባቸው ሲሆን በትራንሰሚሽን ሰብስቴሽን ኮንስትራክሽን ያሉ ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው የጊዜ መርሐ ግብር መሰረት እየተከናወኑ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ በፀጥታ ችግርና በኮሮና በሽታ ምክንያት ለማከናወን አለመቻሉን ወይይቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡
ሦስት ቀናትን በፈጀው የሩብ ዓመት ግምገማ ላይ በኢንጂነሪንግ ዘርፍ በተሰሩ የኢነርጂ ሀብት ልማትና የመነሻ ዲዛይን ስራዎች፣ የጀነሬሽን፣ የትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ቦታ መረጣ፣ ቅየሳና ተያያዥ ስራ እንዲሁም በግል አልሚዎች የሚገነቡ IPP/PPP የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ስራዎችን ላይ ውይይት አከናውኗል፡፡
ከከፋይናንስ ስራዎች አኳያ የኃይል ሽያጭና ሌሎች ገቢዎችን በመሰብሰብ ገቢ የማሳደግ፣ሃብትን በአግባቡ በመጠቀም ወጪን የመቀነስ፣ እና ካፒታል የማሳደግ ስራዎች የተከናወኑ መሆኑንና በንብረት አስተዳደርና አጠቃቀም ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራት በግምገማው ላይ ተነስተዋል፡፡
ከሰው ሃብት ስራዎች አኳያ ፍላጎትን መሰረት ያደረገ የአቅም ግንባታ ስራዎች፣ የስራ አፈጻጸም ምዘና ሰርዓት የሰራተኛ የትምህርት ማስረጃ አግባብነት፣ የሰው ኃብት መረጃ ማሟላትና ማደራጀት፣ የአደረጃጀትና የአሰራር ስርዓት ማሻሻያዎች፣ እንዲሁም የስራ አካባቢ ጤንነትና ደህንነት ስራዎች የተከናወኑ መሆናቸውን በግምገማው ላይ ተጠቅሰዋል፡፡
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ በግምገማው ማጠቃለያ እንደገለፁት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የዝግጅት ጊዜ ቢሆንም የተመዘገበው አፈፃፀም ተቋማዊ ዕቅዱን ለማስፈፀም በሚያስችል መስመር ላይ እየሄድን እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡
ተቋሞ ዘመናዊ አሰራርን ለመተግበር ያስችል ዘንድ የኮርፖሬት ሰርቪስ አስተሳሰብ ከማምጣት አንፃር ጥሩ እንቅስቃሴ እየታየ መሆኑን እና ሥራን በERP /SAP/ ሲስተም ለመስራት እየተደረገ ያለውን ጥረትም የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመው በሩብ ዓመቱ በተለያዩ ምክንያቶች ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸው ሥራዎች ትኩረት ተሰጥባቸው በሁለተኛ ሩብ ዓመት ውስጥ ተካተው መከናወን እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል፡፡
ለግንባታ አስፈላጊ የሆኑ የሲሚንቶ እና ብረታ ብረት ግብዓት አቅርቦት አለመሟላት፣ የፀጥታ ችግር መኖር፣ በፕሮጀክት የግንባታ ስራዎች ላይ እንደችግር የተነሱ ጉዳዮች ሲሆኑ በቀጣይ የታዩ ጉድለቶችን በማረም ሥራን የተሳለጠ ለማድረግ የስራ ተነሳሽነት መፍጠር እንደሚገባ ገልፀው አስፈላጊውን የአቅም ግንባታ መድረኮችን በመፍጠር መስራት እንደሚገባ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አሳስበዋል፡፡
0 Comments