ተቋሙ በጅማ ከተማ አዲስ ህንፃ ሊያስገነባ ነው

Published by corporate communication on

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ሰብስቴሽንና ትራንስሚሽን ኦፕሬሽንና ጥገና ቢሮ በጅማ ከተማ አዲስ ባለ 8 ፎቅ ህንፃ ሊያስገነባ መሆኑን ገለጸ፡፡

የቢሮው ዳይሬክተር አቶ ደረጄ ገዛኽኝ እንደተናገሩት ህንፃው የሚገነባበት 2 ሺህ 500 ካሬ መሬት ቀደም ሲል የዲዝል ጄኔሬተር የሠራተኞች መኖሪያ የነበረ ነው፡፡

የግንባታው ቦታ የአፈር ጥናትና የዲዝይን ሥራዎች መጠናቀቁንና በቅርቡም ጨረታ በማውጣት ወደ ግንባታ ለመግባት የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛል ብለዋል፡፡

ለቅይጥ አገልግሎት ለማዋል ለታሰበው ህንፃ ግንባታ የሚሆን 98 ሚሊዮን ብር በጀት በተቋሙ እንደሚሸፈን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

እንደ አቶ ደረጃ ገለፃ ግንባታው ሲጠናቀቅ እስከ 5ኛ ፎቅ ድረስ ለተለያየ አገልግሎት መስጫነት በማከራየት የተቋሙን ገቢ ለማሳደግ ታቅዷል፡፡

ከ5ኛ ፎቅ በላይ ያለውን ደግሞ ሪጅኑን አሁን ካለበት የኪራይ ህንፃ በማውጣት ለተለያዩ የአስተዳደር እና የአገልግሎት ሥራዎች በመጠቀም የኪራይ ወጪን ለመቀነስ መታሰቡን አቶ ደረጄ አብራርተዋል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

2 + 20 =