ተቋሙን የማዘመን ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለጸ

Published by corporate communication on

ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሚፈለግበት ደረጃ ዘመናዊ እና ተወዳዳሪ ተቋም የማድረግ ሥራዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የተቋሙ የሞደርንናዜሽን ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

የጽ/ቤቱ ዳሬክተር አቶ ሐብታሙ ውቤ እንደገለጹት ተቋሙን ዘመናዊና ተወዳዳሪ ተቋም ለማድረግ በተቋሙ የሥራ አመራር ቦርድ እና በተቋሙ ኃላፊዎች በተሰጠው ትኩረት የሞደርንናዜሽን ጽ/ቤት ተቋቁሞ ወደ ሥራ እንዲገባ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ጽ/ቤቱ የውስጥ አሰራር (Process Modernization) እና ግሪድ ሞደራሊያዜሽን (Grid Modernization) ሁለት ዋና ዘርፎችን በዋናነት በመያዝ የተቋሙን የውስጥ አሠራር፣ እንቅስቃሴዎች፣ የመገልገያ መሣሪያዎች የአረጁ የግሪድ ዕቃዎችን በጥናት ተመርኩዞ በማዘመን በኃይል አቅርቦት ዘርፍ ዘመናዊና  ተወዳዳሪ ተቋም ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል፡፡

በተጨማሪም ቀደም ሲል በተለያዩ የሥራ ክፍሎች በተበታተነ መልኩ ሲካሄዱ የቆዩትን የማዘመን ሥራዎች ወጥነት ባለው መልኩ በኃላፊነት መምራት፣ ማስተባበርና መቆጣጠር ጽ/ቤቱ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል ጥቂቶቹ እንደሆኑ አቶ ሐብታሙ አሰረድተዋል፡፡የተቋሙን ንብረቶች ከመመዝገብ እና ዋጋ ከማውጣት አንስቶ የሰው ኃይልን፣ የፋይናንስ አስተዳደርሩን፣ የፕሮጀክት አስተዳደርን፣ የመገልገያ መሣሪያዎችን አስተዳደር የንብረት አስተዳደርን እና የመረጃ አያያዘን እና የመረጃ ልውውጥን ዘመናዊ፣ ቀልጣፈና አስተማማኝ ማድረግ  ከውስጥ አሰራር ሞድራሊያዜሽን (Process Modernization) የሥራ ዘርፍ የትኩረት አቅጣቻዎች መካከል ተጠቃሾች እንደሆኑ ተጠቁሟል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

nine − 2 =