ብቃትን መሠረት ያደረገ የሙያ ደረጃ ማሻሻያ ስርዓት ሊተገበር ነው

Published by corporate communication on

የኢትዮጵያን ኤሌክትሪክ ኃይል ብቃትን መሠረት ያደረገ የሙያ ደረጃ ማሻሻያ ስርዓት ሊተገብር መሆኑን አስታወቀ፡፡

በአተገባበሩ ዙሪያ ከተቋሙ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች ለተወጣጡ የስራ ኃላፊዎችና ባለሞያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ሥልጠናውን የሠጡት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰው ሃብት ልማት አስተዳደር ዳይሬክተር ዶ/ር ወንደሰን ካሣ እንደተናገሩት አዲስ የተቀረፀውን የተቋሙ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ፣ ራዕይ እና ግቦች ለመተግበር የተለያዩ ሥራዎችን እየተሠሩ ይገኛሉ፡፡

ስትራቴጂውን ለማሣካት የሰው ኃይል ሃብት ልማት፣ አደረጃጀት፣ ቴክኖሎጂ እና የአሰራር ማሻሻያዎች ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ወንደሰን እንዳሉት በተቋሙ ለሰው ሀብት ልማት በተሰጠው ትኩረት ብቃትን መሠረት ያደረገ የሙያ ደረጃ ማሻሻያ ስርዓት ለመተግርበር ስልጠናው ተዘጋጅቷል፡፡

የስልጠናው ዓላማም በተቋሙ ውስጥ ቀጣይነት ባለው መልኩ ብቃት ያለው የሰው ኃይል እንዲኖር የሚያስችል የአሠራር ስርዓትን ለመገንባት የሚረዳ ግንዛቤ መስጠት እንደሆነ ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

ብቃትን መሠረት ያደረገ የሙያ ደረጃ ማሻሻያ ስርዓት በተቋሙ መተግበሩ የተቋሙን ራዕይ እና ስትራቴጂ ግቦች በአመለካከት፣ በእውቀትና በክህሎት የተሞላ የመፈጸም አቅም ያለው የሰው ኃይል ለመፍጠር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ዳይሬክተሩ አስገንዝበዋል፡፡

ሠልጣኞች ከዚህ ስልጠና ያገኙትን እውቀት መሠረት አድርገው በየሥራ ክፍሎቻቸው ብቃትን መሠረት ያደረገ የሙያ ደረጃ ማሻሻያ ስርአት ጥናት የማካሄድና አተገባበሩን የመምራትና የመከታተልና ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው ዶ/ር ወንደሰን ተናግረዋል፡፡

ጥቅምት 12/2012 ዓ.ም

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

two + 7 =