ባለፉት 8 ወራት ከ8 መቶ በላይ ለሚሆኑ ተሸከርካሪዎች የጥገና አገልግሎት ተሰጥቷል

Published by corporate communication on

ባለፉት 8 ወራት ለ8 መቶ 73 ተሸከርካሪዎች የተለያዩ የጥገና አገልግሎቶችን መስጠቱን የተቋሙ የተሸከርካሪዎች ጥገናና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡

በቢሮው የተሸከርካሪ ጥገና አስተዳደር ከፍተኛ ኦፊሰር አቶ ብሩክ እንዳለ እንዳስታወቁት ባለፉት 8 ወራት በተቋሙ ጋራዥ ለ696 ተሸከርካሪዎች ቀላል፣መካክለኛ፣ ከባድ እና የመስክ የጥገና አገልግሎቶችን ለመስጠት ታቅዶ 873 ጥገናዎችን ማከናወን ተችሏል፡፡

ከዚህ ውስጥ 537 ቀላል፣ 244 መካከለኛ፣ 12 ከባድ እንዲሁም 80 የመስክ የጥገና አገልግሎቶች መሰጠቱን ገልፀዋል፡፡

ይህም ከዕቅዱ ጋር ሲመነፃፀር በ177 እንዲሁም ከባለፈው ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃጸር ደግሞ በ136 ተሽከርካሪዎች ብልጫ ማሳየቱን ነው የጠቆሙት፡፡

በዚህም የተቋሙ ጋራዥ ተሽከርካሪዎችን በራስ አቅም በመጠገኑ ተቋሙ ባለፉት 8 ወራት ከ12 ነጥብ 36 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳን ችሏል ብለዋል፡፡

እንደ አቶ ብሩክ ገለፃ ጋራዡ ከሚያከናውናቸው የጥገና ሥራዎች በተጨማሪ ከተቋሙ ውጪ በሆኑ ጋራዦች ጥገና ለተደረገላቸው የተቋሙ 50 ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች በአግባቡ መጠገናቸውን የክትትል እና ቁጥጥር ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ለ936 ተሸከርካሪዎች ቀላልና መካከለኛ ጥገና፣ ለ9 ከባድ፣ ለ100 መስክ ስራ ላይ ላሉ ተሸከርካሪዎች የጥገና ስራ ለማከናወን እንዲሁም በውጭ ድርጅቶች የጥገና ስራ ይከናወንላቸዋል ተብሎ ለታሰቡ 96 ተሸከርካሪዎች የክትትልና የቁጥጥር ሥራዎችን ለማከናወን በዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን አቶ ብሩክ ተናግረዋል፡፡

የተቋሙ ጋራዥ በ2011 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በ36 ሠራተኞች የተለያዩ ጥገናዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ከተሸከርካሪ ጥገና አስተዳደር ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

10 − one =