በ Itsmydam.et የሞባይል መተግበሪያ ከ115 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ ተሰበሰበ

Published by corporate communication on

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የገንዘብ ድጋፍ ለማሰባሰብ የሚያስችል Itsmydam.et የተሰኘው የሞባይል መተግበሪያ ይፋ በተደረገ በአጭር ጊዜ ውስጥ 1058 ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተሳትፈውበት 115,599 የአሜሪካን ዶላር  ተሰብስቧል፡፡

የitismydam የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማጠናቀቅ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የገንዘብ ድጋፍ ለማሰባሰብ የበለጸገ መተግበሪያ ሲሆን ገንዘቡ ሙሉ በሙሉ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ብቻ የሚውል ነው።

መተግበሪው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቪዛ፣ ማስተር ካርድ እና አሜክስን በመጠቀም ከየትኛውም የዓለም ክፍል በአንድ ጊዜ እስከ 10,000 ዶላር ድጋፍ እንዲያደርጉ ያስችላል፡፡

itismydam የሞባይል እና ድህረ ገጽ መተግበሪያ ሙሉ በሙሉ የበለጸገው በኤግል ላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ኃ.የተ.የግ.ማ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አካውንት ተሰባስቦ በቀጥታ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሥራ እንዲውል ይደረጋል፡፡

በተመሳሳይም ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ይፋ በተደረገው www.mygerd.com የተሰኘው ድረ ገጽን መሰረት ያደረገ የድጋፍ ማሰባሰቢያ 182,992 የአሜሪካን ዶላር ተሰብስቧል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

nineteen + 3 =