በፕሮጀክቱ ሁለተኛውን የእንፋሎት ፍለጋ ቁፋሮ ለመጀመር ዝግጅት ተጠናቋል

Published by corporate communication on

የአሉቶ የከርሰምድር እንፋሎት ፍለጋ የሁለተኛ ጉድጓድ ቁፋሮ ለመጀመር ዝግጅት መጠናቀቁን የፕሮጀክቱ የሳይት መሐንዲስ ልዑል አስፋወሰን ገለፁ፡፡

መሐንዲሱ እንደገለፁት የመጀመሪያው ጉድጓድ ቁፋሮ 475 ሜትር ደርሷል፡፡

ለሁለተኛው ጉድጓድ ቁፋሮ የሚውል የመቆፈሪያ ሪግ ተከላ ሥራ የተጠናቀቀ ሲሆን ለቁፋሮው የሚሆን የውሃ አቅርቦትና ሌሎች ዝግጅቶችም መጠናቀቃቸውን ገልፀዋል፡፡

የቁፋሮ ሥራውን የሚያከናውነው ከተለያዩ ሀገራት የተወጣጣው ቡድንም የእርስ በእርስ ትውውቅ በማድረግ ስለሥራ ላይ ደህንነት ገለፃ ተደርጎለታል፡፡

የፕሮጀክቱ የጤና፣ ማህበራዊና አካባቢያዊ ጉዳዮች ተቆጣጣሪ ዛዛ ግሪጎሪያ በፕሮጀክት ትግበራ ወቅት የሥራ ደህንነት ጉዳይ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ በመሆኑ ሁሉም ሠራተኛ በሥራ ቦታ ላይ የሚደርስ ጉዳትን ለመቀነስ በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል፡፡

የሥራ ቦታ ደህንነት ራስን መጠበቅ ብቻ ሳይሆን የስራ ባልደረባንም ከአደጋ የመጠበቅ ግዴታን የሚያካትት በመሆኑ ጥንቃቄ ቀዳሚው የተግባር መመሪያ ሊሆን ይገባል ብልዋል፡፡

የሁለተኛው ጉድጓድ የእንፋሎት ፍለጋ ቁፋሮው በመጪዎቹ ሦስት ቀናት ለመጀመር ዝግጅት ተጠናቋል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

16 + 2 =