በጢስ አባይ ኃይል ማመንጫ የባክአፕ ሲስተሙን አስመስሎ (Modification) በመስራት ማስተካከል ተችሏል

የጢስ አባይ 2 ኃይል ማመንጫ አንድ ዩኒት የሚንቀሳቀስበት ሶፍትዌር በመብራት መቋረጥ ምክንያት በራሱ በመጥፋቱና መልሶ እንዲነሳ የሚያደርግ (BackUp) ፕሮግራም ስላልነበረው ለባክአፕ የሚያግዝ ባትሪ አስመስሎ (Modification) በመስራት ሲስተሙን ማስተካከል መቻሉን የጣቢያው ኃላፊ አቶ ደጀኔ ጉታ ገለፁ፡፡
አቶ ደጀኔ እንደተናገሩት የሞደፊክ ስራ በመሰራቱ የዩኒቱ የኮምፒዩተር ፕሮግራም ያለምንም ችግር መስራት ችሏል፡፡
የፊንጫ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ኃላፊ አቶ ሹመት በላቸው በበኩላቸው ጢስ አባይ እና ፊንጫ ኃይል ማመንጫዎች ባክ አፕ ማድረጊያ ሲስተም ስላልነበራቸው መብራት ሲቋረጥ ዩኒቶቹ ሲሰሩበት የነበረው ፕሮግራም የመጥፋት ዕድል እንደነበረው አስታውሰዋል፡፡
በዚህ የተነሳ ጢስ አባይ የነበረው ፕሮግራም በመብራት መቋረጥ ሲጠፋ ባካፕ ሲስተም ስላልነበረው ፕሮግራሙን እንደገና መጫን አስፈልጎ ነበር፡፡
ሞደፊክ የተሰራው ባካፕ ማድረጊያ ፕሮግራም በተለያየ ምክንያት ቢጠፋ እንኳ ሲስተሙ የመዘገበው ሳይጠፋ እንዲቆይ የሚያደርግ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ሶፍትዌሩ ተገኝቶ ሲስተሙ በተለያዩ የፋይል ማቆያ አማራጮች ባክአፕ ተደርጓል ብለዋል፡፡
0 Comments