በገላን ማከፋፈያ ጣቢያ የአረጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተካሄደ

“ኑ ኢትዮጵያን እናልብሳት” በሚል መሪ ቃል የተጀመረው የ3ኛው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐግብር በገላን ባለ 400/230/132/33/15 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ተካሄደ፡፡
በፊንፊኔ ልዩ ዞን በገላን ከተማ አስተዳደር በመኑሮ ቀበሌ ማህበር በሚገኘው የገላን ማከፋፈያ ጣቢያ ግቢ ውስጥ በተካሄደው የአረጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአዲስ አበባ ሪጅን ትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ኦፕሬሽን ቢሮ ዳሬክተር አቶ ወንደሰን ወ/ማሪያም እንደተናገሩት ለአረንጓዴ አሻራ ሀገራዊ ጥሪው የገላንን ጨምሮ እስከ አሁን በሰበታ አንድ እና በቃሊቲ ጂ.አይ .ኤስ ማከፋፈያ ጣቢያ የአንረጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተከናውኗል፡፡
በቀጣይም በሪጅኑ በሚገኙ በሌሎች ማከፋፈያ ጣቢያዎች መርሃ ግብሩን የማስቀጥል እቅድ እንደተያዘ ተናግረዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ከችግኝ ባሻገር የተለያዩ አበባዎችን በመትከል ማከፋፈያ ጣቢያዎቹን ውብ ፣ ጽዱ እና ምቹ የስራ ቦታ ለማድረግ በሪጅኑ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡
የማከፋፈያ ጣቢያው ኃላፊ አቶ ዓለሙ ዳኛቸው በበኩላቸው 25 ሄክታር ስፋት ባለው የኃይል ማከፋፋያ ጣቢያ ውስጥ ለማስፋፈያ የማይውለውን የውጪኛውን አጥር ተጠግቶ ያለውን ቦታ አረንጓዴ፣ ውብ እና ነፋሻ ለማድረግ መታሰቡን ተናገረዋል፡፡
እንደ ኃላፊው ገለፃ ከ10 ሺህ በላይ ችግኞችን በማቅረብ ፣ የአካባቢውን ህብረተሰብ አስተባብሮ ጉድጓድ በመቆፈር እና ችግኞቹን በመትከል የገላን ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ እገዛ እና ትብብር አድርጓል፡፡
በአረንጓዴ አሻራ ችግኞችን ከመትከል ባሻገር እንዲጸድቁ ተገቢው እንክብካቤ በጣቢያው ሠራተኞች እንደሚደረግ አቶ ዓለሙ አረጋግጠል፡፡
0 Comments