በዱከም እና በሞጆ የተገነቡት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ሊመረቁ ነው

Published by corporate communication on

ለዱከም እና ለሞጆ ከተሞችና እና አካባቢያቸው እንዲሁም በዙሪያቸው ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የኃይል ፍላጎት ምላሽ የሚሰጡ የማከፋፈያ ጣቢያዎች ግንባታ ተጠናቀቀ፡፡

ከአዲስ አበባ በ30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በዱከም ከተማ የተገነባው ባለ 230/15 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የግንባታ፣ የፍተሻ እና የሙከራ ስራ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቋል፡፡
ከአዲሱ የቢሾፍቱ 400/230/15 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ተነስቶ እስከ ዱከም ማከፋፈያ ድረስ 16 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ጥንድ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታም ተከናውኗል፡፡

በሞጆ ከተማ የተገነባው ባለ 230/15 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያም በተመሳሳይ የግንባታ፣ የፍተሻ እና የሙከራ ስራው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቋል፡፡

ሁለቱም ማከፋፈያ ጣቢያዎች ጥንድ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ገቢ መስመር እና አስር ባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች ያሏቸው ሲሆን ሁለት ባለ 50 ሜጋ ቮልት አምፒር ትራንስፎርመሮች ተተክለውላቸዋል፡፡

የማከፋፈያ ጣቢያዎቹ ከጊንጪና ቢሾፍቱ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ጋር በአንድነት በቅርቡ ይመረቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

one × 2 =