በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም የነበራቸው የሥራ ክፍሎች ዕውቅና እንዲሰጣቸው ተወስኗል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ የማኔጅመንት ቡድን በ2013 በጀት ዓመት መልካም አፈፃፀም የነበራቸው የሥራ ክፍሎች ዕውቅና እንዲሰጣቸው ወስኗል።
ማኔጅመንቱ ከሐምሌ22 – 24 ቀን ያካሄደውን ግምገማ ተከትሎ የኃይል ማመንጫዎች ኦፕሬሽን፣ የኃይል ማስተላለፊያዎችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን፣ የሰው ኃይል እና የንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት የሥራ ክፍሎች መልካም አፈፃፀም በማስመዝገባቸው እውቅና እንዲሰጣቸው ተወስኗል።
የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ በውጤታማነት እንዲፈፀምም የሁሉም ሠራተኞችና የሥራ መሪዎች ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማኔጅመንቱ አሳስቧል።
0 Comments