በተቋሙ የድጋፍና እንክብካቤ ትግበራ እየተከናወነ ነው

Published by corporate communication on

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኤችአይቪ መከላከልና መቆጣጠር የሥራ ክፍል የኤችአይቪ/ኤድስ ወረርሽንን ከመከላከል በተጨማሪ የድጋፍና እንክብካቤ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገለጸ፡፡

ኤች.አ.ቪ / ኤድስ በተቋሙ እያደረሰ ያለውን ተፅዕኖ ለመከላከል በፖሊሲ የተደገፈ የድጋፍና ክብካቤ ሥርዐት ዘርግቶ እየሰራ መሆኑን የስራ ክፍሉ አስታውቋል፡፡

ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ሠራተኞች ከኤችአይቪ ጋር የተያያዘ ህመም ከታከሙ ለሕክምና የሚያዋጡት የ10 በመቶ ወጪ መጋራት እንዲቀር ተደርጓል፡፡

እንዲሁም የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ሠራተኞቹ ጤነኛ ሆነው በሥራቸው እንዲቀጥሉ የማድረግ ስራዎችም ተከናውነዋል፡፡

የተቋሙ ሠራተኞች ከደመወዙ በወር ብር 5 ብር በማዋጣት በድምሩ በየወሩ እስከ ብር 35 ሺህ በኤድስ  አስተዋጽኦ (Contrubtion ) አካውንት እየተሰበሰበ ይገኛል፡፡

በተሰብሳቢ ገንዘቡም ቫይረሱ በደማቸው ለሚገኝ 39 (ሰላሳ ዘጠኝ) የተቋሙ ሠራተኞች በየወሩ 7 መቶ ብር ከደሞዝ ጋር በአካውንታቸው እንዲገባ፣ ወላጆቻቸውን በኤች.አ.ቪ / ኤድስ ላጡ 21(ሃያ አንድ) ህፃናት በየወሩ በአሳዳጊዎቻቸው አካውንት ብር 500 እና በትምህርት ዘመኑ መጀመሪያ ላይ ለትምህርት ቁሳቁስ መግዣ በአንድ ልጅ እስከ ብር 1650 ድጋፍ እየተደረገ ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት ከሰራተኞች በወር 35 ሺህ ብር ቢሰበሰብም ወጪ ድጋፍ እየተደረገ ያለው ከሚሰበሰበው በላይ በመሆኑ ልዩነቱ ድጋፉ ከመጀመሩ በፊት በአካውንቱ ውስጥ ከተጠራቀመ ገንዘብ ላይ እየተከፈለ ይገኛል፡፡

በዓለማችን ላይ ኤችአይቪ መከሰቱ ከታወቀበት እ.ኤ.አ. 1981 ጀምሮ ከ32 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሕይወታቸው በኤድስ ምክንያት ያለፈ ሲሆን 38 ሚሊዮን ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው እንደሚገኝ ይገመታል፡፡

በየዓመቱ 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሰዎች አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ እንዳሉና 690,000 ሰዎች ሕይወታቸውን እንደሚያጡ መረጃዎች ያሳያሉ ፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

3 × five =