በተቋሙ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ

Published by corporate communication on

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓልን በዋናው መ/ቤት አክብሯል፡፡

የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል ዘንድሮ ለ14ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን “በአዲስ ምዕራፍ በተሟላ ሉዓላዊነት ለሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ” በሚል መሪ ቃል ዛሬ በመከበር ላይ ይገኛል፡፡

ሰንደቅ ዓላማ የብሔራዊ አንድነት መገለጫ፤ ዜጎች ሀገራዊ ፍቅርና ብሔራዊ ስሜት የሚገልፁበት፤ ታሪካዊ ትስስርና የስነ-ልቦናዊ አንድነት የሚንፀባረቅበት የአንድነትና ህብረት አርማና ምልክት ነው፡፡

የዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችን ብሔራዊ አንድነታችንን እና ሉዓላዊነታችንን እየተፈታተኑ ባሉበት  ወቅት መከበሩ ተናበንና ተደራጅተን በተባበረ ክንድ የተጋረጠብንን የህልውና አደጋ ለመመከትና ለመቀልበስ በጋራ በምንቆምበት አጋጣሚ ስለሆነ ልዩ ያደርገዋል፡፡

የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በየዓመቱ የጥቅምት ወር መጀመሪያ ሰኞ እንዲከበር መወሰኑ ይታወሳል፡፡

ለብሔራዊ አንድነታችንና ሉአላዊነታችን ያለንን ቁርጠኝነት በሰንደቅ ዓላማችን ፊት ዳግም ቃላችንን እናድሳለን!!

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

two × five =