በተቋሙ እየተከናወኑ ባሉ የለውጥ ሥራዎች አበረታች ውጤቶች እየተገኙ ነው

Published by corporate communication on

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እየተከናወኑ ያሉ የለውጥ ሥራዎች አበረታች ውጤት ማስመዝገባቸውን የጊቤ ሁለት የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ተወካይ ሥራ አስኪያጅ አቶ ገበየሁ በላይ ተናግረዋል፡፡

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የጊቤ ሁለት ኃይል ማመንጫ ጣቢያን ከጎበኙ በኋላ በሰጡት በሳል አመራር በርካታ ችግሮች እየተፈቱ መሆኑን ነው አቶ ገበየሁ ገለፁ፡፡

እንደ ዋና አስፈፃሚው ገለፃ ከዚህ ቀደም ሠራተኞች ሲያነሷቸው የነበሩ የጥቅማጥቅም ጥያቄዎች ከዋና ሥራ አስፈፃሚው ጉብኝት በኋላ ምላሽ አግኝተዋል፡፡

ለጣቢያው ሠራተኞች ምቹ የሆነ መኖሪያ ቤት እንዲገነባ በተደጋጋሚ ይቀርብ የነበረው ጥያቄም ምላሽ አግኝቶ አጥር የማጠር ሥራ መጀመሩንም ገልፀዋል፡፡

ለኃይል ማመንጫው ጥቅም ላይ የሚውሉ የመለዋወጫ  ዕቃዎች ግዢ ከዚህ ቀደም የተጓተተና ከዓመታት በላይ ይወስድ እንደነበር የገለፁት ተወካይ ኃላፊው አሁን ግን የመለዋወጫ ዕቃዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ከውጭ ሀገር እንዲገቡ ተደርጎ ተጨማሪ ዩኒቶች ወደ ስራ መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡

የጣቢያው ሠራተኞች አሁን የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚያገኙት በዲዝል ጀነሬተር እንደሆነና በቅርቡ ከጣቢያው ኃይል ማከፋፈያ ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ለማድረግ የዝግጅት ሥራዎች መጀመራቸውን ተወካይ ሥራ አስኪያጁ አስታወቀዋል፡፡

በጊቤ ሁለት ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የኦፕሬሽን ቴክኒሺያን ሆነው ለረጅም ጊዜ ያገለገሉት አቶ ያሬድ ማሞ በተቋሙ ብሎም በጣቢያው እየተከናወኑ ያሉ የለውጥ ሥራዎች ሠራተኞችን ለበለጠ ሥራ ያነሳሱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በተለይም የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በቦታው ተገኝተው የጣቢያው ሠራተኞችን በማወያየት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ  በመስጠታቸው በጣቢያው ሠራተኞች ዘንድ የበለጠ መነቃቃትና የሥራ ወኔ ፈጥሯል ብለዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈፃሚው ወደ ኃላፊነት ከመጡ ወዲህ ጊቤ ሁለትን ጨምሮ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን በተደጋጋሚ በስፍራው በመገኘት ሠራተኞችን በማወያየትና የሥራ መመሪያዎች በመስጠታቸው ፕሮጀክቶች በጥሩ ሁኔታ ሥራቸውን እንዲያከናውኑ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡በተጨማሪም ለዓመታት ሲጋጓተት የነበረውን የገናሌ ዳዋ ሦስት ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የካሳ ክፍያ ከማህብረሰቡ እና ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመወያየት እንዲቋጭ በማድረግ ፕሮጀክቱ በመጪው ነሐሴ 2011 ዓ.ም ኃይል የማመንጨት ሙከራ እንዲያከናውን በማመቻቸት በኩል የጎላ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

20 − 15 =