በተቋሙ ስትራቴጂያዊ ረቂቅ እቅድ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

Published by corporate communication on

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሃገሪቱ የምትፈልገውን የኤሌክትሪክ ፍላጎት  በአስተማማኝ ሁኔታ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ተቋሙ  ከ2012 እስከ 2016  በሚተገብረው  የአምስት  ዓመት ስትራቴጂያዊ ረቂቅ ሰነድ ዙሪያ ከተለያዩ የተቋሙ የስራ ክፍሎች ኃላፊዎች ጋር ውይይት  አካሂዷል፡፡

ረቂቅ ስትራቴጂያዊ እቅዱን ለተሳታፊዎቹ ያቀረቡት የተቋሙ ስትራቴጂያዊ ዝግጅት ቴክኒካል ኮሚቴ አባልና ፀሃፊ አቶ ተማም አፍደል እንደተናገሩት በክፍለ አህጉሩ በኃይል መሰረተ ልማት ትስስር የተፈጠረባቸውን እንዲሁም በቀጣይ ትስስር  የሚፈጠርባቸውን ሃገራት ታሳቢ ያደረገ የ 5 ዓመት ስትራቴጂያዊ ረቂቅ ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡

በመሆኑም ለተዘጋጀው  ስትራቴጂያዊ  ረቂቅ እቅድ  ሰነድ የሚሆኑ አስፈላጊ ግብአቶችን ለመሰብሰብና የጋራ መግባባት ለመፍጠር ታስቦ  የውይይት መድረኩ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡

በውይይቱ የተገኙት ተጨማሪ ግብአቶች በረቂቅ ሰነዱ እንደሚካተቱና  በቀጣይም ከውጭ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ የሚገኘውን ግብዓት በማካተት ለተቋሙ  ሥራ አመራር ቦርድ  በማቅረብ ረቂቅ ሰነዱን የማስጸደቅ ስራ እንደሚከናወን አቶ ተማም አስረድተዋል፡፡

በዚህ ውይይት ከተለያዩ የስራ ክፍል የተወጣጡ ዳሬክተሮች፣ ስራ አስኪያጆችና መካከለኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

ጥቅምት 28/2012 ዓ.ም

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

six − 2 =