በሥራ አስፈጻሚው የሚመራ ቡድን የመስክ ምልከታ ጉብኝት እያደረገ ነው

Published by corporate communication on

 በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ትራንስሚሽን ሰብስትሽን ኦፕሬሽን ሥራ አስፈጻሚ በአቶ ሐብታሙ ውቤ የሚመራ ቡድን  በደቡብ ሪጅን የሚገኙትን ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች እና  የጌቤ 3 ኃይል ማመንጫ ጣቢያ  ላይ የመስክ ምልከታ ጉብኝት እያካሄደ ነው፡፡

ጉብኝቱ  የ2014 በጀት ዓመት አንደኛው ሩብ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም  ግምገማዊ ውይይት አካል እንደሆነ ተነግሯል፡፡

 በሀዋሳ ከተማ በተካሄደው ግምገማዊ በውይይቱ ላይ  የስራ ዘርፉን የውጤት ተኮር የስራ አፈጻጸም ምዘና ስርዓት  ትግበራን በተቀናጀ እና በተናበበ መልኩ ለመተግበር  ከሪጅን ዳይሬክተሮች እና  ከዘርፉ  የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የዘርፉን  የቁልፍ አፈጻጸም መለኪያ(KPI ) እቅድ ግዜ  ወስዶ    ተዘጋጅቶ  እና በውጤት ተኮር ስርዓት ተካቶ  በመተግበሩ  የስራ ዘርፉ ከምንግዜውም የተሸለ አፈጻጸም  ማስመዝገቡ  ተብራርቷል ፡፡

የጉብኝቱን ዋና ዓላማ አስመልክቶ ትራንስሚሽን ሰብስትሽን እና የጄኔሬሽን ኦፕሬሽን የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተር ወ/ሮ ገነት አማን እንደተናገሩት በማከፋፈያ ጣቢያዎቹ ያለው የውጤት ተኮር የምዘና ስርዓትን ወደ ፈጻሚው  ምን ያህል ወርዶ እየተሰራበት እንደሆነ ለማየት እና አካባቢን ለሥራ ምቹ ከማድረግ አንጻር  ምን ይመስላል የሚለውን በመገምገም  አቅጣጫ  ለማስቀመጥ እንደሆነ  አስገንዝበዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ትራንስሚሽን ሰብስትሽን ኦፕሬሽን ሰርቪስ ዳሬክተር አቶ አስማኤል ሙዘይን በበኩላቸው ከሪፖርት በዘለለ መሬት ላይ ያለው ነገር ለመረዳት እና ሠራተኛውን በቅርበት በማነጋገር ቅርርብን ለመፍጠር እንዲሁም  የሚደረግ  ድጋፍን ለመለየት እና እርምት ለመወሰድ  ጉብኝቱ የበለጠ ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም በደቡብ ሪጅን ካሉት ማከፋፈያ ጣቢያዎች አስሩን እና የጌቤ 3 ኃይል ማመንጫ ጣቢያ እንደሚጎበኙ ታውቋል፡፡

በዛሬው እለትም ውሎም  የግቤ 3 ኃይል ማመንጫ ጎብኝተዋል ፡፡

በነገው እለትም ከአስሩ ማከፋፈያ ጣቢያዎች የተቀሩትን በመጎብኘት የመስክ ምልከታ ጉብኝቱ እንደሚጠናቀቅ የተያዘው መርሃ ግብር ያስረዳል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

seven + 8 =