በሀገር ደረጃ ሊከሰት የሚችለውን የኃይል መቋረጥ ለመቀነስ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሰሩ ነው

Published by corporate communication on

በሀገር ደረጃ ሊከሰት የሚችለውን የኃይል መቋረጥ  ለመቀነስ የሚ ያግዙ የሲስተም ማሻሻያዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን የኃይል ማመንጫዎች ኦፕሬሽን ሥራ አስፈፃሚ አቶ እያየሁ ሁንዴሳ ተናግረዋል፡፡

አቶ እያየሁ እንደገለፁት በጊቤ 3 ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የገዥ ሲስተም መቆጣጠሪያ (Governor System Regulator) ተግባራዊ በማድረግ የሀገር አቀፍ ኃይል መቋረጥን መቀነስ ተችሏል፡፡

ከዚህ ቀደም በአንድ ቦታ ላይ የሚከሰት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር መቋረጥ ለሀገር አቀፍ የኃይል አቅርቦት መቋረጥ ምክንያት ይሆን ነበር ያሉት አቶ እያየሁ፣ የኦፕሬሽን ሲስተሙን በማዘመን ችግሩን መቅረፍ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡

የሀገር አቀፍ ኃይል መቋረጥ በተደጋጋሚ እንዳይከሰት ለማድረግ ሰፊ የሲስተም ማሻሻያዎች እየተከናወኑ መሆኑን አቶ እያዩ ተናግረዋል፡፡

ስራ አስፈፃሚው እንደተናገሩት የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን አጠቃላይ የኃይል ቁጥጥር ዑደት ለማዘመን ይረዳ ዘንድ ኮሪያ ፓወር ኮርፖሬሽን ከተሰኘ ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈፅሞ ወደ ሥራ ለማገባት እየተሰራ ነው፡፡

በተጨማሪም የሀገር አቀፍ ኤሌክትሪክ መቋረጥ በሚያጋጥምበት ወቅት ከሌሎች ጊዜያት በአጠረ ጊዜ ወደ ሥራ ለማስገባት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ  ነው ብለዋል፡፡

በጊቤ አንድ እየተስተዋለ ያለውን የመጠባበቂያ ዲዝል ጀነሬተር ችግር ለመቅረፍም የተሻለ አቅም ያለው ጀነሬተር ማቅረብ ተችሏል፡፡

የበለስ እና የጊቤ አንድ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን የኦፕሬሽን ሲስተም ለማዘመንም በዘርፉ የካበተ ልምድ ካላቸው የውጭ ሀገራት ኩባንያዎች ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸውን ሥራ አስፈፃሚው አስታውቀዋል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

two + nine =