ስርቆትን ለማስቀረት ከህብረተሰቡ ጋር በቅርበት እየተሰራ ነው

Published by corporate communication on

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የደቡብ  ሪጅን ትራንስሚሽን ሰብስቴሽን ኦፕሬሽን ቢሮ በሪጅኑ እየተስፋፋ  የመጣውን  የታወር ብረት  እና የኬብል ስርቆት ወንጀል ለመከላከል  የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገለጻ፡፡

የቢሮው ዳይሬክተር  አቶ አለማየው  ዘበርጋ እንደተናገሩት   የታወር ብረት  እና የኬብል ስርቆት ወንጀል በሪጅኑ በተደጋጋሚ ከሚከስትባቸው አከባቢዎች መካከል የምእራብ አርሲ ዞን አንዱ ነው ብለዋል፡፡

በዚህ አካባቢ ስርቆቱን ለማስቀረት ከተወሰዱት አማራጮች መካከል አንዱ ከዞኑ አስተዳደር እና  የጸጥታ አካለት ጋር በመሆን  ታወር  እና ኬብል በሚያልፋቸው አካባቢዎች ለሚገኙ አርሶ አደሮችና ነዋሪዎች  ንብረቱን እንዲጠብቁ ኃላፊነት የመሠጠት  ስራ ነው፡፡

በዚህም አበረታች ጅምር ውጤቶች እየተገኙ አንደሚገኙ አቶ አለማየው አስገንዝበዋል፡፡

ሆኖም በአንዳንድ ሪጅኑ በሚሸፍንባቸው ዞኖች የሚገኙ የስራ ሃላፊዎች የስርቆት ወንጀሉን ለመከላከልና  ተባብሮ ለመስራት ያላቸው ፍለጎት አናሳ መሆንንና በቂ ድጋፍ እና እግዛ አለማድረግ  ወንጀሉን እያስፋፋው እንደሚገኝ ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡

ችግሩን  ለመቀነስ እና ለማስቀረት  ከአካባቢው የአሰተዳደር፣የጸጥታ አካለት እና ከህብረተሰቡ ጋር ተደጋጋሚ ውይይት ማካሄድ፣በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ድርጊቱን የማገለጥ እና  ግንዛቤ የማሳደግ ስራዎችን ይበልጥ ማጠናከር እንዲሁም በሪጅኑ  የሰርቆት ወንጀሉን  በቅርበት እና በሃላፊነት የሚከታተል የህግ ባለሞያ መመደብ ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ ሃላፊው አስረድተዋል፡፡

ሪጅኑ በተለያየ ቮልቴጅ መጠን በሚያስተዳድራቸው  19 ማከፋፈያ ጣቢያዎች እና 3,200 ኪ.ሜ  ርዝመት ባለው ኃይል  ማስተላለፊያ መስመር ከኦሮሚያ ክልል ምእራብ አርሲን ፣ ሻኪሶን፣ ቦረና  ዞኖች  እና  ከደቡብ ክልል ጌዶን፣ ወላይታን እና  ሀላባን ዞኖች ጨምሮ   የሲዳማ  ክልልን ሙሉ ለሙሉ  እንዲሁም  የሀዲያ- ሆሳዕና  ዞንን በከፊል  እየሸፈነ ይገኛል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

five × 4 =