ራዕይ እና ተልዕኮ

ራዕይ

በ 2022 ዓ.ም  አለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ሀገራዊና ክፍለ-አህጉራዊ የኃይል ፍላጎት ሊሸከም የሚችል ተመራጭ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅሪቢ ተቋም መሆን፡፡

ተልዕኮ

ዘላቂና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል መሰረተልማት በመገንባት እና በማስተዳደር የኤሌክትሪክ ኃይልን  በጅምላ በመሸጥ እና በመግዛት  የሀገር ኢኮኖሚ እድገት የሚያስፈልግ የኤሌክትሪክ ኃይል ማቅረብ፡፡

ዕሴቶች

  • ግልፅነትንና ተጠያቂነትን ማስፈን
  • የሰው ኃይል አቅም ግንባታን ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ መንቀሳቀስ
  • ሠራተኞች የድርጅቱ ዋነኛ ሐብት መሆናቸውን ተገንዝበን ተገቢውን አያያዝ ማድረግ
  • የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማትን ህግና ደንብ ማክበር
  • ያሉ ሐብቶችን በአግባቡ መጠቀም
  • ለአካባቢ ጥበቃ ተገቢውን ትኩረት መስጠት
  • ማህበራዊ ኃላፊነትን መወጣት
  • በራስ ኃይል ግንባታዎችን በማከናወን አገራዊ ተጠቃሚነትን ከፍ ማድረግ
  • አዳዲስ የፈጠራ ሐሳቦችን ማበረታታት፡፡