ሪጅኑ ዓመታዊ የስራ አፈፃፀሙን ዛሬ ገምግሟል

Published by corporate communication on

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የምስራቅ ሪጅን ትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ኦፕሬሽንና ጥገና መምሪያ ዓመታዊ የስራ አፈፃፀሙን ዛሬ ገምግሟል፡፡

በግምገማው መጀመሪያ ላይ ለሀገር ሰላምና ሉዓላዊነት ለተሰው የመከላከያና የፀጥታ አካላት የ1 ደቂቃ የህሊና ፀሎት የተደረገ ሲሆን በሪጅኑ የሚገኙ የ12ቱም ሰብስቴሽን ኃላፊዎች፣ የጅግጅጋ እና ድሬዳዋ ንዑስ ሪጅን ኃላፊዎች የአፈፃፀም ሪፖርቶች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

ሪጅኑ በመደበኛና አስቸካይ ጥገናዎች የያዘውን ዕቅድ ሙሉ በሙሉ ማሳካቱና ለሌሎች ሪጅኖች መልካም ተሞክሮ ሊሆን የሚችል ቢሮዎችን ለሥራ ምቹ የማድረግ ሥራ መከናወኑም ተገልጿል፡፡

የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ጋሻው እንድርያስ በግምገማው ላይ እንደተናገሩት የዓመቱ አፈፃፀም በመልካም የሚጠቀስ ቢሆንም ከዚህም የተሻለ ለማከናወን ሁሉም በትጋት እንዲሰራ አሳስበዋል፡፡

በአዲሱ በጀት ዓመት ጉድለቶችን በመሙላት ለላቀ ሥራ እንዲነሳሱ በማሳሰብ  የስራ አፈፃፀም ግምገማ ስርዓትና  የእድገት ውድድርን በተመለከተ ከሠራተኞች ለተነሱ ጥያቄዎችም  ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ከፍተኛ የአፈፃፀም ውጤት ላመጡ 2 ወንድና 1 ሴት ሰራተኞች እንዲሁም በጡረታ ለተገለሉ አንድ  ሰራተኛ  የዕውቅና ምስክር ወረቀት  ተሰጥቷል።

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

nine − 2 =