ሠራተኞቹ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ

Published by corporate communication on

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ትራንስሚሽን ሰብስቴሽን ኦፕሬሽን የ2013 ዓ.ም አፈፃፀም በመገምገም እና የ2014 ዓ.ም እቅድ ላይ በመወያየት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አጋርነታቸውን ለመግለፅ የደም ልገሳ አደረጉ፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የሪጅን ትራንስሚሽን ጥገና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዐቢይ መኮንን እንደገለፁት በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙት የኃይል ተሸካሚ ታወር ብረቶች ስርቆት ለኦፕሬሽን ሥራ እንቅፋት ሆኗል፡፡

በመሆኑም ሁሉም የሪጅኑ ሠራተኞች ባገኙት አጋጣሚ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ ሊሰሩና  እንደተቋም ከክልል፤ ከዞን እና ከከተማ መስተዳድሮች ጋር በቅርበት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

የሪጅኑ ሰብስቴሽን ኦፕሬሽን እና ጥገና ስራ አስኪያጅ አቶ ሚሊዮን ቡልቲ በበኩላቸው በስራ ክፍሉ ሰፊ የጥገና እና የኢንስፔክሽን ስራዎች እንደተከናወኑ ገልፀዋል፡፡

የሪጅኑ አመራሮችና ሰራተኞች በ2014 ዓ.ም እቅድ ላይ የተወያዩ ሲሆን የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ሲሳይ ለእቅዱ መሳካት የሁልም ሰራተኞች ርብርብ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም የነበራቸው ሰራተኞች የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡ ለሪጅኑ አገልግሎት የሚሰጥ የሞባይል መተግበሪያ ላበለፀጉት ለአቶ ማሩፍ ሚፍታየሞባይል ሽልማት አበርክቷል፡፡

ሰራተኞቹ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ካደረጉት የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ ከጅማ ደም ባንክ ጋር በመነገር 21 ዩኒት ደም ለግሰዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአዳማ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሠራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት 32 ዩኒት ደም ለግሰዋል፡፡

የጣቢያው ሠራተኞች የሀገርን ህልውና ለማስጠበቅ እየተዋደቀ ለሚገኘው ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የአንድ ወር ደመወዛቸውን ድጋፍ ከማድረጋቸው በተጨማሪ ነሐሴ 11 ቀን 2013 ዓ.ም አዳማ ከተማ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ደም ባንክ ቅርንጫፍ ደም በመለገስ ድጋፋቸውን አድርገዋል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

17 − eleven =