ከወላይታ ሶዶ-አዲስ አበባ የተዘረጋው ሁለተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ከወላይታ ሶዶ-አዲስ አበባ የተዘረጋው ሁለተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር በነባሩ የጊቤ III- ወላይታ ሶዶ- አዲስ አበባ ታወር ወይም ማማ ላይ በተጨማሪ የተዘረጋ መሆኑን የ400 ኪ.ቮ ፕሮጀክት ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ መሐመድ ሽኩር ተናግረዋል፡፡ በፕሮጀክቱ በዋናነት የኤሌክትሪክ ኮንዳክተር እና ኢንሱሌተር ዝርጋታ እንዲሁም የተለያዩ መሳሪያዎች ገጠማ መከናወኑን ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡ እንደ ሥራ ተጨማሪ ያንብቡ…

ዲ.ኬ.ቲ ኢትዮጵያ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት የኮሮና መከላከያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ዲ.ኬ.ቲ ኢትዮጵያ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ሠራተኞች የሚውል ግምታቸው ከ430 ሽህ ብር በላይ የሆኑ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል፣ ሳኒታይዘር እና ሌሎች ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ፡፡ በርክክብ ሥነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ እንደገለፁት ዲ.ኬ.ቲ ኢትዮጵያ ከግድቡ ግንባታ ጀምሮ እስካሁን ተጨማሪ ያንብቡ…

ተቋሙ የፕሮጀክቶችን ማማከርና የዲዛይን ዝግጅት አቅሙ እያደገ መጥቷል

የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮችንና የማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክቶችን በራስ ኃይል የማማከር አቅሙ እያደገ መምጣቱን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጅነሪንግ ሥራ አስፈፃሚ አቶ አንዱዓለም ሲዓ ገለፁ፡፡ ሥራ አስፈፃሚው እንደገለፁት ተቋሙ ከ66 እስከ 500 ኪሎ ቮልት ያሉትን ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችንና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ግንባታ የማማከር ስራን ላለፉት 20 ዓመታት ሲያከናዉን ቆይቷል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተጨማሪ ያንብቡ…

በ2012 በጀት ዓመት ከ15 ሺህ ጊጋ ዋት ሰዓት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ተችሏል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በተጠናቀቀው የ2012 በጀት ዓመት 15,192 ነጥብ 11 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት መቻሉን የኃይል ማመንጫዎች ኦፕሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ በጽ/ቤቱ የኃይል ማመንጫዎች ኦፕሬሽን ቴክኒካል ድጋፍ እና አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ሰናይ ገ/ጊዮርጊስ እንዳስታወቁት በበጀት ዓመቱ 16,165 ነጥብ 48 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ዕቅድ ተይዞ ተጨማሪ ያንብቡ…

የጊቤ 3 የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግድብ ውሃ መለቀቅ ተጀመረ

የጊቤ 3 የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ በክረምቱ ዝናብ እየሞላ በመምጣቱ ውሃ መለቀቅ ተጀምሯል፡፡ ከግድቡ በየደረጃው የሚለቀቀው ዉሃ በታችኛው ተፋስስ ላይ ቅፅበታዊ ጎርፍ እንዳይከሰት ለመቆጣጠር ነው፡፡ ወደ ግድቡ የሚገባውን ውሃ ሁሉ እንደመጣ ላለመልቀቅና የተመጠነ የውሃ ፍሰት እንዲኖር በማድረግ ሊያጋጥም የሚችለውን ጉዳት ለማስቀረት ከአደጋ መከላከልና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽንና ከደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ተጨማሪ ያንብቡ…

Facebook