ተንሳፋፊ ሳርና የመለዋወጫ አቅርቦት እጥረት የጣቢያው ስጋት እየሆኑ ነው ተባለ

የበለስ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ተንሳፋፊ ሳርና የመለዋወጫ አቅርቦት ስራውን እያስተጓጎለበት መሆኑን የጣቢያው ኃላፊ ገለፁ፡፡ ኃላፊው አቶ ፍቃዱ ደምሴ እንደገለፁት ወደ ጣቢያው የውሃ መቀበያ እየተገመሰ የሚመጣው ተንሳፋፊ ሳር ለኃይል ማመንጫው የኦፕሬሽን ሥራ ከፍተኛ ስጋት እየሆነ ነው፡፡ ተንሳፋፊ ሳሩ ከሐምሌ 9-11 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ የኃይል ማመንጫ ጣቢያውን እስከማስቆም ደርሶ እንደነበረ የገለፁት ተጨማሪ ያንብቡ…

አዋሽ III የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለጊዜው አገልግሎቱን አቋረጠ

በአዋሽ III የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ የጎርፍ መጥለቅለቅ በማጋጠሙ ከቅዳሜ ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ጣቢያው ለጊዜው አገልግሎት ማቋረጡን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአዋሽ II እና III ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዲሳሳ ገልሜሳ አስታውቀዋል፡፡ ላለፉት 49 ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየውና 32 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የአዋሽ ተጨማሪ ያንብቡ…

ከ1 ሺህ 3 መቶ ኪ.ሜ በላይ የኃይል ማስተላለፊያ መስመርና 14 የማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክቶችን ግንባታ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው

በ2013 በጀት ዓመት የ1 ሺህ 304 ነጥብ 2 ኪ.ሜ የማስተላለፊያ መስመርና 14 የማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን የኃይል ማስተላለፊያ መስመርና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ፕሮግራም መምሪያ አስታወቀ፡፡ የመምሪያው ኃላፊ ወ/ሮ ጽዮን ብርሃኑ እንዳስታወቁት በአሁኑ ሰዓት በመላው ሀገሪቱ የተለያየ የኪሎ ቮልት መጠን ያላቸው 14 የማስተላለፊያ መስመር እና 34 ተጨማሪ ያንብቡ…

ከሀገር ውስጥ የኃይል ሽያጭ እና ከፋይበር ኦፕቲክስ ኪራይ ከ8 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዷል

በተያዘው የ2013 በጀት ዓመት ከሀገር ውስጥ የኃይል ሽያጭ እና ከፋይበር ኦፕቲክስ ኪራይ ከ8 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን የማርኬቲንግና ቢዝነስ ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡ በተያዘው የበጀት ዓመት 12 ነጥብ 9 ቢሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት(12 ሺህ 900 ጊጋ ዋት ሰዓት) የኤሌክትሪክ ኃይል ለሀገር ውስጥ ተጠቃሚዎች በማቅረብ 8 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ያንብቡ…

የአዘዞ – ጭልጋ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር እና ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ እየተፋጠነ ነው

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማዕከላዊ ጎንደር ዞን እየተገነባ የሚገኘው የአዘዞ – ጭልጋ ባለ 230/33 ኪ. ቮ. የኃይል ማስተላለፊያ መስመር እና ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ አንድ አዲስ ባለ 230/33 ኪ. ቮ. ከፍተኛ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ እና 40 ኪ ሜ. ርዝመት ያለው የባለ 230 ኪ. ተጨማሪ ያንብቡ…

አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶችን በማስወገድ ከ33 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት የማይሰጡ የተለያዩ ንብረቶችን በማስወገድ በ2012 በጀት ዓመት 33 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን የተቋሙ ንብረት አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡ የቢሮው ስራ አስኪያጅ አቶ ታደሰ ዳዲ እንደገለፁት ገቢው የተገኘው አገልግሎት የማይሰጡ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ አልሙኒየም፣ መዳብ፣ የተለያዩ የዕቃ ማሸጊያ ጣውላዎች፣ ያገለገሉ የተሸከርካሪ ጎማዎች እና የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በማስወገድ ተጨማሪ ያንብቡ…

ለታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሠራተኞችና የፀጥታ አካላት 40 ሰንጋዎች በስጦታ ተበረከተ

የአማራና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች  የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሠራተኞችንና የፀጥታ አካላትን  በስፍራው በመገኘት አበረታቱ። የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት በሙሉ ርዕሳነ መስተዳድሮቹ ያላቸውን አድናቆት በመግለፅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እንደተናገሩት የአባይ ተፋሰስን ለመጠበቅ ክልሉ በአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ላይ በንቃት ተሳትፎ ተጨማሪ ያንብቡ…

ሁሉም ተቋራጭ የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጣ ይገባል ተባለ

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሊት በታቀደው መሰረት እንዲከናወን ሁሉም ተቋራጮች ተናበው እንዲሰሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትርና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር አብርሃም በላይ አሳሰቡ። ዶ/ር አብርሃም የግድቡን ሥራዎች ከተመለከቱ በኋላ ከተቋራጮች ጋር ሲወያዩ እንደተናገሩት ተናቦ በመስራት የታሰበውን ውጤት ለማምጣት ሁሉም ሊረባረብ ይገባል። በመሆኑም የቅድመ ኃይል ተጨማሪ ያንብቡ…

የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ግድብ ግንባታ 35 በመቶ ደረሰ

የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ግድብ ግንባታ 35 ነጥብ አንድ በመቶ መድረሱን የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ። የሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ሞቱማ መቃሳ የኮይሻን ግድብ ግንባታ በተመለከተ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ፕሮጀክቱ እስከ ነሐሴ 2012 ዓ.ም ድረስ አፈጻጸሙ 35 ነጥብ አንድ በመቶ ደርሷል። ሁለት ሺህ 160 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ተጨማሪ ያንብቡ…

ከወላይታ ሶዶ-አዲስ አበባ የተዘረጋው ሁለተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ከወላይታ ሶዶ-አዲስ አበባ የተዘረጋው ሁለተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር በነባሩ የጊቤ III- ወላይታ ሶዶ- አዲስ አበባ ታወር ወይም ማማ ላይ በተጨማሪ የተዘረጋ መሆኑን የ400 ኪ.ቮ ፕሮጀክት ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ መሐመድ ሽኩር ተናግረዋል፡፡ በፕሮጀክቱ በዋናነት የኤሌክትሪክ ኮንዳክተር እና ኢንሱሌተር ዝርጋታ እንዲሁም የተለያዩ መሳሪያዎች ገጠማ መከናወኑን ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡ እንደ ሥራ ተጨማሪ ያንብቡ…

Facebook