የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የኢትዮጵያውያን ህልውና መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናገሩ

የታላቁ ኢትዮጵያ  ህዳሴ ግድብ ግንባታ የኢትዮጵያውያን ህልውና መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ።     የግድቡን ግንባታ አስመልክቶ በስካይላይት ሆቴል በተዘጋጀ ሀገር አቀፍ ሲምፓዚየም  ላይ  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደተናገሩት  የዓባይ ተፋሰስ የሃገሪቱን ሁለት ሶስተኛውን የውሃ ተፋሰስ የሚሸፍን በመሆኑ ዓባይን የማልማት ጉዳይ የህልውና ጉዳይ ነው። ግድቡ መላው ኢትዮጵያውያን ተጨማሪ ያንብቡ…

ዋና ሥራ አስፈፃሚውና አምባሳደሩ የመልካ ዋከና የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያን ጎበኙ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር የመልካ ዋከና የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያን ጎበኙ፡፡ ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ አሸብር ባልቻ ጣቢያው ከ30 ዓመት በላይ ያገለገለ በመሆኑ የማሻሻያ ሥራዎች እንደሚፈልግ ለአምባሳደሩ ገልፀውላቸዋል፡፡ የጣቢያውን አቅም ለማሳደግ ቀደም ሲል የመግባቢያ ሥምምነት መፈረሙን በማስታወስ የተጀመሩት ቴክኒካል ጥናቶች ሂደቶች እንዲፋጠኑና ለማሻሻያ ስራው ተጨማሪ ያንብቡ…

ሴቶች ለመልካም ማህበረሰብ ግንባታ ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ ነው ተባለ

ሴቶች በተቋማዊ እና ሀገራዊ ግንባታ ካላቸው ግንባር ቀደም ሚና ባለፈ ለመልካም ማህበረሰብ ግንባታ የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የንብረትና አገልግሎት ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ስመኝ አያሌው ዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀን ምክንያት አድርገው ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት ሴቶች በልጆች አስተዳደግ እና በቤተሰብ አስተዳደር ያላቸው ችሎታ እና አስተዋይነት ለመልካም ማህበረሰብ ግንባታ ተጨማሪ ያንብቡ…

የኤሌክትሪክ ኃይልን ፍትሐዊ በሆነ መልኩ ተደራሽ ማድረግ ይገባል – የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር

የጃዊ – በለስ ባለ 132/33 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ  መስመርና ማከፋፈያ ጣቢያ ትናንት ተመርቋል፡፡   በምርቃት ሥነ – ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አቅሙን በየጊዜው እያሳደገ የሀገሪቱን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት እየሰራ ያለው ሰራ የሚበረታታ ነው፡፡   ይሁን እንጅ በክልሉ ተጨማሪ ያንብቡ…

የማከፋፈያ ጣቢያው ግንባታ 68 በመቶ ደርሷል

በማሻ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የማሻ – መቱ ባለ 230/33 ኪ.ቮ. የኃይል ማስተላለፊያ መስመር እና ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት አጠቃላይ አፈጻጸም 68 በመቶ መድረሱን የማከፋፈያ ጣቢያው የሳይት ተቆጣጣሪ መሐንዲስ አቶ ፍቃዱ ሁጤሳ ገለፁ፡፡ መሐንዲሱ እንደገለፁት ፕሮጀክቱ አንድ አዲስ ባለ 230/33 ኪ. ቮ. ከፍተኛ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ እና 161 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው የባለ ተጨማሪ ያንብቡ…

በቀጣዮቹ 10 ዓመታት የማመንጨት አቅምን ከ17 ሺህ ሜጋ ዋት በላይ ለማድረስ እየተሰራ ነው

በቀጣዮቹ 10 ዓመታት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅምን ከ17 ሺህ ሜጋ ዋት በላይ ለማድረስ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የዋና ሥራ አስፈፃሚ የቴክኒክ አማካሪ አስታወቁ፡፡ አማካሪው ኢንጂነር አንዳርጌ እሸቴ እንደገለፁት በአሁኑ ሰዓት በሀገሪቱ ያለዉ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም 4 ሺህ 528 ሜጋ ዋት ደርሷል፡፡ በቀጣዮቹ 5 ዓመታት 13 ሺህ ተጨማሪ ያንብቡ…

የሚዛን ማከፋፈያ ጣቢያ በሙሉ አቅሙ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል

ከአዲስ አበባ በ561 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ በደቡብ ክልል በቤንቺ ማጂ ዞን በሚዛን ከተማ የሚገኘው የሚዛን 132/66/33/15 ኪ.ቮ. ከፍተኛ ማከፋፈያ ጣቢያ ተገቢውን አገልግሎት እየሠጠ ይገኛል፡፡ የጣቢያው ተወካይ ኃላፊ ወ/ት ታደለች ተረፈ እንደተናገሩት በ1998 ዓ.ም. ከቦንጋ ማከፋፈያ ጣቢያ 132 ኪ.ቮ. በመቀበል ለሚዛን ከተማና ለአካባቢው በ15 እና 33 ኪ.ቮ. ወጪ መስመሮች ኃይል በመስጠት ተጨማሪ ያንብቡ…

ጣቢያው አገልግሎቱን በብቃት፣ በጥራትና በተገቢው መንገድ እየሠጠ ነው

የማስፋፈያ እና የአቅም ማሳደግ ሥራዎች የተሠሩለት የመቱ ባለ 230/66/33/15 ኪ.ቮ. ማከፋፈያ ጣቢያ ተገቢውን አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን የማከፋፈያ ጣቢያው ኃላፊ አቶ ሰለሞን ጎሳ ገለጹ፡፡ አቶ ሰለሞን እንደገለፁት በ1984 ዓ.ም. ከሶር ኃይል ማመንጫ በ66 ኪ.ቮ. መስመር ኃይል በመቀበል ለመቱ እና ለአካባቢው በ15 ኪ.ቮ. ኃይል በመስጠት በይፋ ሥራ የጀመረው ማከፋፈያ ጣቢያው እስከ 2002 ተጨማሪ ያንብቡ…

በአባ ወረዳ አዲስ ባለ132/33 ኪ.ቮ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ሊገነባ ነው

በደቡብ ክልል ዳውሮ ዞን በአባ ወረዳ በ48 ሚሊዮን ብር ወጪ አዲስ ባለ 132/33 ኪ.ቮ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ሊገነባ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ሰብስቴሽንና ትራንስሚሽን ኦፕሬሽንና ጥገና ቢሮ አስታወቀ፡፡ የቢሮው ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ገዛኽኝ እንደገለፁት 1998 ዓ.ም. ተገንብቶ አገልግሎት  ሲሰጥ የቆየው የአባ ባለ 132/33 ኪ.ቮ. ማከፋፈያ ጣቢያ በ2012 ዓ.ም. በደረሰበት የመሬት ተጨማሪ ያንብቡ…

Facebook