የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈፃፀም 76.35 በመቶ ደረሰ

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈፃፀም 76 ነጥብ 35 በመቶ መድረሱን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን፣ በመስኖ ልማት፣ በኢነርጂ እንዲሁም በተፋሰስና የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ዙሪያ የ2013 የሩብ ዓመት የስራ ዕቅድ አፈፃፀምን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በተያዘው 2013 ዓ.ም ሁለቱ ተርባይኖች ኃይል እንዲያመነጩ ለማስቻል በሩብ ተጨማሪ ያንብቡ…

ግድቡ አሁን ከያዘው በ3 እጥፍ የሚበልጥ ውሃ እንዲይዝ ይደረጋል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ በዘንድሮው ዓመት አሁን ከያዘው በ3 እጥፍ የሚበልጥ ውሃ እንደሚይዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ  በጋራ የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጉብኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው የግድቡ ግንባታ ሂደት በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ መመልከታቸውንም ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሕዳሴ ግድብ ተጨማሪ ያንብቡ…

በፕሮጀክቱ ንብረቶች ላይ እየተፈፀመ ያለው ስርቆት ተቋሙን ለተጨማሪ ወጪ ዳርጎታል

የኢትዮ- ኬንያ ባለ 500 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ተደጋጋሚ የስርቆት ወንጀሎች እየተፈፀሙበት እንደሚገኝ የኢትዮ – ኬንያ የኃይል ማስተላለፊያ መስመርና ኮንቨርተር ጣቢያ ፕሮጀክት የግንባታ አስተባባሪ ገለፁ፡፡ አስተባባሪው አቶ ሰይፉ ፈይሳ እንደገለፁት በኢትዮጵያ በኩል የሚገነባው የ433 ኪሎ ሜትር የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፡፡ ይሁን እንጅ በወላይታ ዞን አንዳንድ ተጨማሪ ያንብቡ…

በማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ የቆጣሪ ገጠማ ሥራ በመከናወን ላይ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ የቆጣሪ ገጠማ ስራ በማከናወን ላይ መሆኑን በተቋሙ የስማርት ሜትር ፕሮጀክት ቢሮ ስራ አስኪያጅ አስታወቁ፡፡ ሥራ አስኪያጇ ወ/ሮ ሃይማኖት ተፈራ እንደገለጹት ተቋሙ 130 በሚሆኑ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ የቆጣሪ ገጠማ ስራ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ የቆጣሪዎቹ መገጠም የተቋሙ ደንበኞች ለተጠቀሙት ኃይል ትክክለኛውን ክፍያ እንዲከፍሉ ለማድረግ ተጨማሪ ያንብቡ…

ሚኒስትሩ የኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታን ጎበኙ

የውሃ፣መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ዋና ጸሃፊ ከቬራ ሶንግዌ ጋር በመሆን የኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታንና በሥራ ላይ የሚገኘውን ጊቤ ሶስት የውሃ ኃይል ማመንጫን ጎበኙ፡፡ ጉብኝቱ ኢትዮጵያ ያሏትን የውሃ ሃብቶች ለዘላቂ እድገትና ለዜጎች ህይወት መሻሻል እንዴት በአግባቡ እየተጠቀመች እንደሆነ ለማየት አጋጣሚ እንደፈጠረላቸው ተጨማሪ ያንብቡ…

ሚኒስትሩ የታላቁ ህዳሴ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታን ጎበኙ

የውሃ፣መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ዋና ጸሃፊ ከቬራ ሶንግዌ ጋር የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታን ጎበኙ፡፡ ዋና ፀሐፊዋ ስለግድቡና ስለግንባታው ሂደት በሚኒስትሩ ገለፃ ተደርጎላቸው ግንባታውን እየተዘዋወሩ ተመልክተዋል። ከጉብኝቱ በኋላም በግድቡ ግዝፈትና በግንባታው ሂደት ውስብስብነት መደነቃቸውን ዋና ፀሀፊዋ ከቬራ ሰንግዌ ለሚኒስትሩ ተጨማሪ ያንብቡ…

የወላይታ ሶዶ ኮንቨርተር ጣቢያ የሙከራ (commissioning) ስራ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል

የወላይታ ሶዶ ባለ 500 ኪሎ ቮልት የኮንቨርተር ስቴሽን ፕሮጀክት የሙከራ ስራ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡ በፕሮጀክቱ የሰብሰቴሽን ኢንቻርጅ ባለሙያው አቶ ሃብታሙ ግርማ እንደገለፁት የኮንቨርተር ጣቢያውን የግንባታ ስራ በማጠናቀቅ በአሁኑ ወቅት የኮሚሽኒንግ ስራው በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ከወላይታ ሶዶ ከተማ 7 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እየተገነባ የሚገኘውን የኮንቨርተር ጣቢያ ፕሮጀክት የሙከራ ስራ ተጨማሪ ያንብቡ…

የተቋሙን የብድር ዕዳ ጫና ለማቃለል እየተሰራ ነው

የተቋሙን የብድር ጫና ለማቃለል እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የፋይናንስ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደመረ አሰፋ አስታወቁ፡፡ ሥራ አስፈፃሚው እንዳስታወቁት ተቋሙ የተሰጡትን ተልዕኮዎች ለመወጣት ከተለያዩ የፋይናንስ ምንጮች በመደበኛ የወለድ ምጣኔ የሚገኙ ብድሮችን (Commercial loan) እና አነስተኛ የወለድ ምጣኔና ረዘም ያለ የመክፈያ ጊዜ ያላቸው ብድሮችን (Concessional loans) በመጠቀም የተለያዩ የኃይል መሰረተ ልማት ተጨማሪ ያንብቡ…

በዱከም እና በሞጆ የተገነቡት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ሊመረቁ ነው

ለዱከም እና ለሞጆ ከተሞችና እና አካባቢያቸው እንዲሁም በዙሪያቸው ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የኃይል ፍላጎት ምላሽ የሚሰጡ የማከፋፈያ ጣቢያዎች ግንባታ ተጠናቀቀ፡፡ ከአዲስ አበባ በ30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በዱከም ከተማ የተገነባው ባለ 230/15 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የግንባታ፣ የፍተሻ እና የሙከራ ስራ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቋል፡፡ከአዲሱ የቢሾፍቱ 400/230/15 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ተጨማሪ ያንብቡ…

የኃይል ሽያጭ ስምምነት ተደረገ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኃይል ሽያጭ ስምምነት አደረጉ፡፡ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሸብር ባልቻ እና የኢትየጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈረው ተሊላ ተፈራርመዋል፡፡ ትናንት በተካሄደው የፊርማ ሥነ-ስርዐት ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሸብር ባልቻ እንደተናገሩት ስምምነቱ ተቋማቱ በተሻለ ተጨማሪ ያንብቡ…

Facebook