ማስታወቂያ

Published by corporate communication on

የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ሐምሌ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ለአሉቶ ፕሮጅክት ቢሮ በኮንትራት በተለያዩ የስራ መደቦች ማለትም በሴመንቲንግ ኢንጂነሪንግ 2ኛ፤ መድ ኢንጂነር 2ኛ፤ ጂኦተርማል ሪዘርቬየር ኢንጂነር 2ኛ፤ ዌል ቴስቲንግ ኢንጂነር 1ኛ፤ ሪግ ኤልትሪሺን፤ ሪግ ሜካኒክ፤ ሜዥርመንት ቴክኒሺያን፤ ዲሪሊንግ ኢንጂነር 3ኛ፤ ድሪሊንግ ኢንጂነር 2ኛ፤ ጂኦሎጂስት 2ኛ እንዲሁም ጂኦሎጂስት 3ኛ የስራ መደቦች ላይ አወዳድሮ ለመቅጠር ማስታወቂያ ማውጣቱ እና አመልካቾችም በተቀመጠው መስፈርት መሰረት በኦን ላይን መመዝገባቸው ይታወቃል፡፡

ስለሆነም በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ያመለከታችሁ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአንድ ሳምንት ውስጥ የትምህርት መረጃችሁን እና የስራ ልምዳችሁን በኢሜል አድራሻችን  hr.hiring@eep.com.et እንድትልኩልን እናሳውቃለን፡፡

 ማሳሰቢያ

አመልካቾች ኢሜይል በምታደርጉበት ወቅት በጉዳዩ (Subject) ላይ የተወዳደራችሁበት የስራ መደብ  ጠቅሳችሁ እንድትልኩልን እናሳስባለን፡፡


0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

3 × 1 =