ሚኒስትሩ የታላቁ ህዳሴ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታን ጎበኙ

Published by corporate communication on

የውሃ፣መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ዋና ጸሃፊ ከቬራ ሶንግዌ ጋር የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታን ጎበኙ፡፡

ዋና ፀሐፊዋ ስለግድቡና ስለግንባታው ሂደት በሚኒስትሩ ገለፃ ተደርጎላቸው ግንባታውን እየተዘዋወሩ ተመልክተዋል።

ከጉብኝቱ በኋላም በግድቡ ግዝፈትና በግንባታው ሂደት ውስብስብነት መደነቃቸውን ዋና ፀሀፊዋ ከቬራ ሰንግዌ ለሚኒስትሩ ገልፀውላቸዋል።

በጉብኝቱ ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ እንዲሁም የተቋሙ የኃይል ማመንጫዎች ግንባታ ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሰፋ ንጉሴ ተገኝተዋል።

በኢትዮጵያውያን የገንዘብ ድጋፍ በመገንባት ላይ የሚገኘው የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አጠቃላይ አፈፃፀም 76 ነጥብ 3 በመቶ ላይ ደርሷል።

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

four × 3 =