ለግድቡ በየደቂቃው በአማካይ 17 ዶላር እየተሰበሰበ ነው፤ በአምስት ቀን ውስጥ ከ111 ሺህ ዶላር በላይ ተሰብስቧል

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ የሚደረግበት ድረ ገፅ www.mygerd.com ይፋ ከሆነ ዛሬ አምስተኛ ቀኑ ነው፡፡
እስካሁን ድረስ ከ876 ኢትዮጰያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ 111,540 ዶላር ተሠብስቧል ። 45 ሰዎች ደግሞ ለልገሳው የሚሆን ዘመቻ በማድረግ ላይ ናቸው።
በአማካይ በየሰዓቱ 1 ሺህ ዶላር ለግድቡ እየተለገሰ ሲሆን በየደቂቃው ደግሞ 17 ዶላር መሰብሰብ ተችሏል፡፡ እንዲህ ዓይነት የድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕላትፎርም ሲዘጋጅ በኢትዮጵያ ይህ የመጀመሪያው እንደሚሆን እምነት አለን፡፡
www.mygerd.com ድረ-ገፅ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባሉበት አካባቢ ሆነው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ ለማድረግ እና አሻራቸውን ማሳረፍ ለሚፈልጉ የተዘጋጀ ድረ-ገፅ ነው ፡፡
የማይደበዝዝ አሻራዎን ያሳርፉ፤ ሌሎችንም እንዲሳተፉበት ይጋብዙ!!
0 Comments