ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ

Published by corporate communication on

የኮይሻ የኤሌክትረክ ኃይል ማመንጫ  ፕሮጀክት ሰራተኞች  ለሀገር መከላከያ ሰራዊት 1,466, 721.000  ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን የፕሮጀክቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አባይነህ ጌትነት ገለጹ፡፡

ድጋፉ   በሁለት ምእራፍ የተከናወነ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር 413,640.00  ብር  በሁለተኛው ዙር  ደግሞ 1,053,081.00  ብር  ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የደቡብ እዝ ተወካይ ማስረባቸውን ምክትል ሥራ አስኪያጁ  ተናግረዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ሰራተኞች ከዚህ ቀደምም ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከልን የ386,610.00  ብር   ድጋፍ ማድረጋቸው ን አቶ አባይነህ አስታውሰዋል፡፡

በራስ ተነሳሽነት እና  በበጎ ፈቃድ  የሚደረገው ድጋፍ የሚመሰገን እና በሌሎችም ተጠናክሮ  ሊቀጥል እንደሚገባ ምክትል ሥራ አስኪያጁ ጠቁመዋል፡፡

በደቡብ ከልል በኮንታ ልዩ  ወረዳ እና በጎፋ ዞን መለኮዛ ወረዳ መካከል አየተገነባ የሚገኘው የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት የግድበ ሙሌት ግንባታ ፣የኃይል ማመንጫ ቤት ግንባታ ፣የውኃ  ማስተንፈሻ ቁፋሮ  እና ለግንባታ  የሚያስፈልጉ የተለያዩ ማሺነሪዎችን  እና ሌሎች ስራዎችን በማከናወን አጠቃላይ የፕሮጀክቱ አፈጻጸም 45 በመቶ ደርሷል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

1 × 5 =